ጎሕ ቤቶች ባንክ አ.ማ. ጥበቃ እና ሴት ፈታሽ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አግልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር/004/26
ጎሕ ቤቶች ባንክ አ.ማ ጥበቃ እና ሴት ፈታሽ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አግልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው የሚወዳደሩ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. ከፌደራል ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቅጥር/employment/ ለ2018 ዓ.ም የታደስ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዶቹ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ ቅጅ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የቲን የምስክር ወረቀት እና ከገቢዎች ሚኒስቴር ከግብር ነፃ መሆናቸውንና ጨረታ መሳተፍ የሚችሉ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከ 15/10/ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት የማይመለስ ሶስት መቶ ብር /300.00/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በዋና መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ /Bid Bond/ ብር 50,000.00 ቢያንስ ለ120 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ በባንክ በተመሰከረለት የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
6. የጨረታው መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
7. ተጫራች በስራው/በዘርፉ ለ3 ዓመታትና ከዚያ በላይ የቆየ መሆን አለበት፤ ከሶስት ዓመት በታች ልምድ ያለው ድርጅት ተቀባይነት አይኖረውም
8. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፤
- በስልክ ቁጥር 011 668 6833 / 011 668 7376 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ወይም በአካል በመቅረብ መረጃ ማግኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ቦሌ ጃፓን ኢምባሲ አርማህ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ የባንኩ የሰው ሃብትና ሰፕላይ ቼይን መምሪያ ማግኘት ይችላሉ።
Tender details
- Deadline: 2026-07-07
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-07-07 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Goh Betoch Bank
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Jun 21, 2026
- Posted at: 2026-06-22T10:28:09.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.