የቢፍቱ አዳማ ሆስፒታል የጥበቃ ሥራ፣ የፅዳት ሥራ እና የግቢ ውስጥ እና አካባቢ አረንጓዴ ልማት እንክብካቤ ሥራ (Outsource) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

ለአንደኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ 

የቢፍቱ አዳማ ሆስፒታል በ2019 የበጀት ዓመት፡-

  1. የጥበቃ ሥራ
  2. የፅዳት ሥራ እና
  3. የግቢ ውስጥ እና አካባቢ አረንጓዴ ልማት እንክብካቤ ሥራ (Outsource) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ኤጀንሲዎች/ነጋዴዎች መወዳደር ትችላለችሁ።

  • የ2018 ዓ.ም የታደሰና ህጋዊ ንግድ ፍቃድ በዘርፉ ያላችሁ እንዲሁም የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈለ።
  • ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆን መረጃ ማቅረብ የሚችል።
  • በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  • ለጥበቃ ሥራ ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለበት።
  • ለጥበቃ ሥራ አገልግሎት የሚውለውን ዕቃ ይዞ ይቀርባል።
  • ለፅዳት ሥራ ከአዳማ ከተማ የምግብ ዋስትና እና የሥራ ፈጠራ ክህሎት /ጥቃቅንና  አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ/ ቢሮ የድጋፍ ደብደቤ ማምጣት የሚችል እና በፅዳት ሥራ ላይ በ(1MX) የተደራጀ መሆን አለበት።
  • ለፅዳት ሥራ አገልግሎት የሚውለውን ዕቃ ይዞ ይቀርባል።
  • ለግቢ ውስጥ እና አካባቢ አረንጓዴ ልማት እንክብካቤ ሥራ ከአዳማ ከተማ የምግብ ዋስትና እና የሥራ ፈጠራ ክህሎት/ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ/ቢሮ የድጋፍ  ደብዳቤ ማምጣት የሚችል እና በግቢ ውስጥ እና አካባቢ አረንጓዴ ልማት እንክብካቤ ሥራ ላይ በ(1MX) የተደራጀ መሆን አለበት።
  • ለግቢ ውስጥ እና አካባቢ አረንጓዴ ልማት እንክብካቤ ሥራ አገልግሎት የሚውለውን ዕቃ ይዞ ይቀርባል።
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ኮፒና ኦርጅናል ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ማቅረብ አለባቸው።
  • የቁጥር ስርዝ ድልዝ ያለው፣ የማይታይ የጨረታ ሰነድ ወይም የዋጋ ዝርዝር ተቀባይነት የለውም።
  • ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ዋጋ 10% ማስያዝ የሚችል።
  • ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሆስፒታሉ ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ክፍል ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ 500(አምስት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  • የጥበቃ ሥራ ጨረታው የሚከፈተው በ25/0/2018 ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • የፅዳት ሥራ ጨረታው የሚከፈተው በ26/10/2018 ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • የግቢ ውስጥ እና አካባቢ አረንጓዴ ልማት እንክብካቤ ሥራ ጨረታው የሚከፈተው  በ29/10/2018 ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • ከዚህ በፊት ከመንግሥታዊ ድርጅት በስነ-ምግባርም ሆነ በሌላ ምክንያት ደብዳቤ የተፃፈበት ድርጅት መወዳደር አይችልም።
  • ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ ብቻ መሆን አለበት።

የጨረታ ማስከበሪያ

  • ለእያንዳንዱ ሥራ የጨረታ ማስከበሪያ 30,000.00 (ሰላሣ ሺህ)ብር በSinqe” ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝና ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።

መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ  የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 11-77 58 92 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

ቢፍቱ አዳማ ሆስፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-07-06
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
  • Bid opening: 2026-07-06 14:30
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: የቢፍቱ አዳማ ሆስፒታል
  • Bid bond: 30,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Jun 22, 2026
  • Posted at: 2026-06-23T09:36:36.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders