በሐረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግሰት ማረሚያ ኮሚሽን ስር ለሚገኙ ህግ ታራሚዎች የበሰለ ምግብ የሚያቀርቡ በንግድ ዘርፉ ተመሳሳይ የንግድ ፍቃድ ያለው እና በጥቃቅንና አነሰተኛ የተደራጁ ማህበራትን አወዳደሮ ከአሸናፊው ጋር ውል ለመፈፀም ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ግዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የበሰለ የምግብ አቅርቦት የሚያቀርብ

በሐረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግሰት ማረሚያ ኮሚሽን ስር ለሚገኙ ህግ ታራሚዎች የበሰለ ምግብ የሚያቀርቡ በንግድ ዘርፉ ተመሳሳይ የንግድ ፍቃድ ያለው እና በጥቃቅንና አነሰተኛ የተደራጁ ማህበራትን አወዳደሮ ከአሸናፊው ጋር ውል ለመፈፀም ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች ተፈላጊውን የበሰለ የምግብ አይነት ብዛትና መጠን የሚገልፅ የጨረታ ሠነድና መመሪያ የማይመለሰ ብር 100 በመክፈል ሠነዱን መግዛት ይኖርባቸዋል።

2. በንግድ ዘርፉ ተመሳሳይ የንግድ ፍቃድ ያለው እና ተጫራቾች በጥቃቅንና አነሰተኛ የተደራጁ ህጋዊ ማህበር እና ሌሎች የግል የምግብ አብሳዮች ማቅረብ የሚችሉ ህጋዊ ነጋዴዎች ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።

3. የበሰሉ ምግቦችን ከማቅረብ ጋር በተያያዘ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ቲን ነበር ያላቸው።

4. ህጋዊ የምስክር ወረቀት እና የሚፈለግባቸውን የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፋላቸው ማረጋግጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማሰከበሪያ ቢድ ቦንድ 3,000.00/ሶስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በሞዴል 85 ማሰያዝ አለባቸው።

6. ጨረታ ሰነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ10 ለተከታታይ ቀን ውስጥ ይሸጣል።

7. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከሰኔ 15/2018 ዓ/ም አንስቶ ለ10 የተከታታይ ቀናት ብቻ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ሰኔ 26/2018 ዓ/ም በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዢ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል።

8. የበሰለ ምግብ አቅርቦቱ የሚያሸንፈው ጊዜ ከሐምሌ1/2018 ዓ/ም እሰከ ታህሳስ 30 /2019 ዓ/ም 6 ወር ይሆናል።

9. አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

10. መ/ቤቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ በመሙላት ለዚህ ስራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ዶክመንታቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ሰኔ 26/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይችላሉ። የበሰለ ምግብ አቅራቢዎች ህጋዊ ማስረጃ ያላቸው መሳተፍ እንደሚችሉ ያሳስባል።

12. ተጨማሪ መረጃ የስልክ ቁጥር 025 666 0541 ፖስታ ሳ.ቁ 31

በሐረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-07-03
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-07-03 10:30
  • Region: Hareri
  • Publishing entity: Harari Peoples Regional Government Prisons Commission
  • Bid bond: 3,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Jun 22, 2026
  • Posted at: 2026-06-23T09:43:26.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders