የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለከባድ እና ለቀላል ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ለሰርቪስ መኪናዎች አገልግሎት የሚውል ጂፒኤስ (GPS) ከነገጠማ ተጫራቾችን በጨረታ እወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ጂፒኤስ ከነገጠማው ግዥ ለመፈፀም የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ሥ.ኮ/ብግጨ/19/2018

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2018 በጀት ዓመት ለከባድ እና ለቀላል ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ለሰርቪስ መኪናዎች አገልግሎት የሚውል ጂፒኤስ (GPS) ከነገጠማ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ዝርዝር መስፈርት (Specification) መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ እወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ ማስረጃ፣ የቫት ተመዝጋቢ፣ ቲን፣ የፍሊት ማናጅመንት ብቃት ማረጋገጫ እና በEGP የአቅራቢዎች ሊስት የተመዘገበ ስለመሆኑ ማስረጃ መቅረብ ይኖርበታል። እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ በሚገኘው ፋፋ የምግብ አ.ማ ጀርባ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ግዥ ክፍል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሰላሣ ሺህ ብር ብቻ) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታ ዋጋ ለ60 (ስልሳ) ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል። ጨረታው ሰኔ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ይከናወናል።

ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-

ስልክ፡- +251 91 198 4467 ወይም +251 91 056 7578

ፋክስ 011 442 1312

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-07-03
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-07-03 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Agricultural Business Corporation
  • Buyer address: ከሳሪስ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ማህበር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jun 24, 2026
  • Posted at: 2026-06-24T08:17:11.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders