የግል ድርጅት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የተለያዩ ንብረቶችን መሸጥ ይፈልጋል
Description
የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ስሙ ከዚህ በታች የተመለከቱት ድርጅት በግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 1268/204 አንቀጽ 2 መሰረት ከሠራተኛው መደበኛ የወር ደመወዝ ላይ ተገቢውን የጡረታ መዋጮ ቀንሰው እና የድርጅቱን ድርሻ መዋጮ ጨምረው ለግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ፈንድ ገቢ ባለማድረጉ አስተዳደሩ በአዋጅ ቁጥር 1268/2014 አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 13 በተሠጠው ስልጣን እና አዋጁን ለማስፈጸም በወጣው መመሪያ ቁጥር 1086/2017 መሠረት የድርጅቱን ሃብት በግልጽ ጨረታ በመሸጥ ውዝፍ ጡረታ መዋጮ ዕዳው እንዲሰበሰብ ወስናል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
|
ተራ ቁጥር |
ውዝፍ የጡረታ መዋጮ ዕዳው የሚፈለግበት ድርጅት ሥም |
በቀጣይ የሚታሱብ ወለድ እና ቅጣት ሳይጨምር ክድርጅቱ የሚፈለገው የጡረታ መዋጮ ዕዳ መጠን በብ |
የካርታ ቁጥር/የሊዝ ይዞታ ምስክር ወረቀት ቁጥር/ የማሽነሪው አይነት |
የቦታው ስፋት በካሬ ሜትር
|
የድርጅቱ ሃብት የሚገኝበት ኣድራሻ
|
የጨረታ መነሻ ዋጋ
|
|
1 |
ቴዎድሮስ ደበላ ኢጋኖ (ጅማ ደጊቱ ሆቴል) |
8,092,113,44 |
2308/2002
|
670 ካሬ ሜትር |
ጅማ ከተማ ቦሳ ኪቶ ቀበሌ |
44,408,087.70
|
|
2 |
ቤዝዓለም ኔትዌር ኃ/የተ/የግ/ማህ |
3,621,898.70
|
የሶፍትና ወረቀት ማምረቻ ማሽነሪ |
|
አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ ወረዳ 7 ልዩ ስሙ ኢንድስትሪ ሰፈር |
24,519.220.27
|
1. ስለሀብቱ አሻሻጥ ከአስተዳደሩ የግዥ ዳይሬክቶሬት ወይም ከህግ ጉዳዮች ዳይሬከቶሬት መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት ከግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ብር 200.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ በግልጽ በማስፈር በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ አድርገው አድራሻው ለግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና መ/ቤት በማለት አስፍረው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሠዓት እንዲሁም ከሠአት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሠዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በግዢ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው የግልጽ ጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች በቅድሚያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/1ዐኛውን በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
5. ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሠዓት ተዘግቶ በ4፡15 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስተዳደሩ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
6. ተጫራቾች ይዞታውን በግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና መ/ቤት በሚያመቻቸው ፕሮግራም በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
7. አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግዥው ዋጋ ጋር ታስቦ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባለት 15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ በመከፈል ሃብቱና መረከብ አለበት፡፡
8. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ የማይከፍል ከሆነ ለጨረታው በዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ለአስተዳደሩ ገቢ ሆኖ የጨረታው አሸናፊነቱ ይሠረዛል፡፡
9. ከሽያጩ ጋር በተያያዘ የሚከፈሉ ግብርና ታክሶች፣ የስም ማዛወሪያ እንዲሁም ሌሎች ማናቸውም ህጋዊ ወጪዎች በገዢ ይሸፈናሉ፡፡
10. አስተዳደሩ ስለሀብቱ አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ መገናኛ ቦሌ ከ/ከተማ አስተዳደር ፊት ስፌት
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111570333/0111574906
የግል ድርጅት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር
Tender details
- Deadline: 2026-07-18
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-07-18 12:00
- Bid opening (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡15 ሠዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Private Companies Employees Social Security Agency
- Buyer address: መገናኛ ከቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፊት ለፊት ወይም ከሙሉጌታ ዘለቀ ህንጻ አጠገብ
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jul 01, 2026
- Posted at: 2026-07-01T07:51:03.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.