ታህሰብ የንግድ ስራዎች አክሲዮን ማህበር ሕንጻ ውስጥ የተለያዩ የጅብሰን ብሎክ ስራዎች እቃ አቅርቦ የሚሰራ ባለሙያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በታህሰብ የንግድ ስራዎች አክሲዮን ማህበር ሕንጻ ውስጥ የተለያዩ የጅብሰን ብሎክ ስራዎች እቃ አቅርቦ የሚሰራ ባለሙያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው።
2. የዘመኑን ግብር ለመክፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ።
4. የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ይሆናል።
5. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) ብር በመከፈል ዘወትር ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡30 ድረስ አክሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት በመቅረብ የጨረታ ሰነዱንና የተጫራቾች መመሪያ መግዛት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ11ኛ (አስራ አንደኛው) የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአክሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (በታህሰብ የንግድ ስራዎች አክሲዮን ማህበር )ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
9. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።
10. አሸናፊው የጨረታ ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አስር ) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርቦ የስራ ውል መዋዋል አለበት።
11. አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ - አዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ኮልፌ (mና) ተራ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0112 79 30 65
ታህሰብ የንግድ ስራዎች አክሲዮን ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-07-14
- Bid closing time: 16:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡30 ድረስ
- Bid opening: 2026-07-15 14:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ (አስራ አንደኛው) የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Tahseb Business S.C.
- Bid bond: 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር)
- Bid document price: 500 (አምስት መቶ) ብር
- Published: Jul 05, 2026
- Posted at: 2026-07-06T07:34:39.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.