ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር የአጎና ህንፃ ጥገና ስራ ተጫራቾችን አወዳድሮ የጥገና ስራ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

CN/NCB/39/2018

የድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር የአጎና ህንፃ ጥገና ስራ ተጫራቾችን አወዳድሮ የጥገና ስራ ማሰራት ይፈልጋል። በዚህም ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የህንፃ ተቋራጭ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ወይም የአገልግሎቱ ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ፖስታ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።

የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ ዓርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-10፡30) እና ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጠዋት ማግኘት ይቻላል:: የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል።

ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ጠዋት ድረስ ማስገባት ይችላሉ:: ጨረታው በዚሁ ዕለት በ4፡30 ጠዋት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል:: ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል።

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ

ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ

ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር 011-1-569992

አዲስ አበባ

ኢትዮጵያ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-21
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-07-21 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Commercial Nominees P.L.C.
  • Buyer TIN: 0000958158
  • Buyer address: ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Jul 05, 2026
  • Posted at: 2026-07-06T11:23:11.000Z
  • Buyer website: https://commercialnominees.com/

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders