ቦናንዛ አዲስ ሆቴል ኃ.የተ.የግ.ማኅበር በቃሊቲ፣ በጃክሮስ እና በገርጂ የጥበቃ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ የጥበቃ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የጥበቃ አገልግሎቱን ማሠራት ይፈልጋል
Description
የቦናንዛ አዲስ ሆቴል ኃ/የተ/የግ/ማኅ እና እህት ኩባንያዎች የጥበቃ አገልግሎት ገዢ የጨረታ ማሰታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ቦአ/ቢድ/0001/2018
ድርጅታችን ቦናንዛ አዲስ ሆቴል ኃ/የተ/የግ/ማኅበር የሆቴል አገልግሎት በሚሰጥበት ዋና መሥሪያ ቤት እና በእህት ኩባንያዎቹ የሥራ ቦታዎች ማለትም በቃሊቲ በጃክሮስ እና በገርጂ የጥበቃ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ የጥበቃ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የጥበቃ አገልግሎቱን ማሠራት ይፈልጋል።
ስለሆነም
1. ከላይ የተጠቀሰውን አገልግሎት ለመስጠት ፍላጎት ብቃት እና ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች ከኤድናሞል ወደዓለም ሲኒማ በሚወስደው መንገድ ከገልፍአዚዝ ሕንጻ ፊትለፊት በሚገኘው የሆቴሉ አስተዳደር ቢሮ በአካል በመቅረብ ከሰኔ 29 እስከ ሐምሌ 06 ቀን ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ። የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ የሚከናወነው ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ከቀኑ 11፡30 ሰዓት እና ቅዳሜ ከ ጠዋቱ 2፡30 እስከ ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ነው።
2. በጨረታው ስመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ እና ቫት ሰርተፍኬት ኮፒ ግብር ስለመክፈሉ የሚያረጋግጥ ወቅታዊ ደብዳቤ ክሊራንስ ከአገር ውስጥ ገቢ
- ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር የተሰጠ የታደስ የስራ ፈቃድ ኮፒ
- ከፌደራል ፖሊስ የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ የታደሰ ፈቃድ ኮፒ
- ለሆቴል የጥበቃ ስራ 8ኛ ክፍል ከዚያ በላይ የትምህርት ማስረጃ እንዲሁም ለሌሎቹ ድርጅቶች 4ኛ ክፍልና ከዚያ በላይ ማቅረብ የሚችሉ የጥበቃ ሠራተኞችን ማቅረብ የሚችል
- ለሆቴል የጥበቃ ሥራ ከመደበኛው የአማርኛ የሥራ ቋንቋ (ማንበብ | መጻፍ፤ መስማትና መናገር የሚችሉ) በተጨማሪ በእንግሊዘኛ ቋንቋ መሠረታዊ በሆነ መልኩ መግባባት የሚችሉ ለሌሎች እህት ኩባንያዎች በመደበኛው የአማርኛ የሥራ ቋንቋ (ማንበብ፤ መጻፍ፤ መስማትና መናገር የሚችሉ) መግባባት የሚችሉ የጥበቃ ሠራተኞችን ማቅረብ የሚችል
- በጥበቃ ሥራ ሙያ በቂ ስልጠና ያላቸው የጥበቃ ሠራተኞችን ማቅረብ የሚችል
- ለሆቴል የጥበቃ ሥራ ወንድም ሆነ ሴት የጥበቃ ሠራተኞች አካላዊ ቁመናቸው በስፖርት የዳበረ ፣ ደመግቡ /መልከኛ/ እና ንቃትና ቅልጥፍና ያላቸው፣ ጤነኛና ከደባል ሱሶች የጸዳች የጥበቃ ሠራተኞችን ማቅረብ የሚችል
- የንብረት አጠባበቅ ላይ ተገቢውን ጥንቃቄና ምዝገባ ማድረግ የሚችሉ የጥበቃ ሠራተኞችን ማቅረብ የሚችል
- ለሆቴል የጥበቃ ሥራ 6/ስድስት/ የሴት የጥበቃ ሠራተኞች ማቅረብ የሚችል
- በድርጅቱ የሥራ መሪዎች የሚሰጣቸውን የሥራ መመሪያዎች ተግባራዊ የሚያደርጉ የጥበቃ ሠራተኞችን ማቅረብ የሚችል፣
3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማሰከበሪያ ዋስትና ብር 100,000 (መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በቅድም ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በቦናንዛ አዲስ ሆቴል (Bonanza Addis Hotel) ስም አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ወይም ተመሳሳይ ይዘት ባለው ፎርም ላይ በመሙላት እስከ ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በጨረታው ሰነድና መመሪያ ላይ በተቀመጠው የፖስታ አቀራረብ መሠረት በሰም በታሸገ ፖስታ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ በማድረግ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ። ጨረታው ሰኞ ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቦናንዛ አዲስ ሆቴል ይከፈታል።
5. የጨረታ አሸናፊ የሆነው የጥበቃ አገልግሎት ሰጪ አሸናፊነቱ በተገለጸ በ10 ቀናት ውስጥ ውል መፈረም ይጠበቅበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል።
6. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ቦናንዛ አዲስ ሆቴል ኃ/የተ/የግ/ማህበር
አዲስ አበባ
Tender details
- Deadline: 2026-07-13
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-07-13 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: BONANZA ADDIS HOTEL PLC
- Buyer TIN: 0072265975
- Bid bond: 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
- Published: Jul 05, 2026
- Posted at: 2026-07-06T11:50:44.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.