የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሀረር ፊደራል ፖሊስ ሆስፒታል እና አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ Supply and Fix Cable ladder and Cable tray ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/SF/91/2026

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሀረር ፊደራል ፖሊስ ሆስፒታል እና አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ Supply and Fix Cable ladder & Cable try ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

.

 

የዕቃው ዓይነት

የፕሮጀክት ስም

 

የጨረታ ቁጥር

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ ማስከበሪያ

 

Supply and Fix Cable ladder & Cable tray

ሀረር ፊደራል ፖሊስ ሆስፒታል እና ግንባታ ፕሮጀክት

DCE/ SF/91/2026

ሐምሌ 15/2018 . 400 ሰዓት

ሐምሌ 15/2018 . 415 ሰዓት

50,000.00

 

ስለሆነም፡-

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ፣ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ.ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው። 

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ በሠንጠዥ በተገለፀው መሠረት በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ለ120 (አንድ መቶ ሃያ) Calendar days ፀንቶ የሚቆይ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘውትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መ.ኮ.ድ ግቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር እና ብዛት መሠረት መሆን ይኖርበታል።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴከኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መ.ኮ.ድ ግቢ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር፡- 0114-40-34-34 ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72 E-mail አድራሻ info@dce-et.com 
የድህረ ገፅ አድራሻ፡- www.dce-et.com 
ፖ.ሳ.ቁ፡- 3414 ፋክስ ቁ.0114-40-04-71/0114-
የመከላከያ ኮንስትራክሸን ኢንተርኘራይዝ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-22
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-07-22 10:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Defense Construction Enterprise (DCE)
  • Buyer address: ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Jul 08, 2026
  • Posted at: 2026-07-08T07:59:36.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders