ፀደይ ባንክ አ.ማ. የመኖሪያ ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ለመጀመርያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ፀደይ ባንክ አ.ማ አቶ ገረመዉ አይናለም ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዘውን በምስራቅ ጎጃም ቀራንዮ ከተማ ቀበሌ 01 የካርታ ቁጥር k_926 በአቶ ገረመዉ አይናለም ስም ተመዝግቦ የሚገኝዉን የመኖሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች በመገንዘብ መጫረት እንዲችሉ ይጋብዛል።
1. የቤቱ የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 427,438.65 (አራት መቶ ሃያ ሰባት ሽህ አራት መቶ ሰላሳ ስምንት ከ65 ብር ብቻ የሆነ
2. ተጫራቾች የቤቱን ጨረታ መነሻ ዋጋ ብር ¼ (በጥሬ ገንዘብ) ወይም በሲፒኦ በጸደይ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
3. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተዉ አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ብቻ ይሆናል
4. በጨረታዉ የሚሳተፈዉ በህገ ሰዉነት ያገኝ ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ጽሁፍ ወደም መተዳደሪያ ደምብ፤ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘበት ቦም ዘገባ የምስከር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ዉክስና ማቅረብ አለበት።
5. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ዉስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጨረታ ይሸነፈውን ንብረት መረከብ ይኖርበታል አሸናፊዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታዉ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
6. በጨረታ ለተሸነፉ ተጫራጮች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
7. የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛዉ ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከቤቱ ጋር የተያያዙ ማናቸዉም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፡ ግብር፤ ተጨማሪ አሴት ታክስ 15% እና ከስም ዝዉዉሩ ጋር የሚገናኙ ማንኛዉንም ወጭዎች ገዢ ይሸፍናል/ ይከፍላል። ዉዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረዉና የክፍያ ጊዜዉ ላልደረሰ የሊዝ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር እንዲዋዋል ይደረጋል።
8. ተጫራቾች ቤቱን/ድርጅቱን/ በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ።
9. ጨረታዉ የሚካሄደዉ ሀምሌ 27/2018 ከጠዋቱ 3.00---5.00 የተጫራቾቾ ምዝገባ ከ5.00 እስከ ቀኑ 6.00 ጫረታ በደበረ ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 02 ዲስትሪክት 03ኛ ፎቅ ይሆናል።
10. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሱ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠተበቀ ነዉ።
- ለተጨማሪ መረጃ፡- ፀደይ ባንክ ደበረማርቆስ ዲስትሪክት
- ስ.ቁ 0587712034/ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል።
Tender details
- Deadline: 2026-08-03
- Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Published: Jul 08, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.