የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪከት ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በድርድር ሽያጭ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የድር ድር ሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪከት ለኬኛ ጠቅላላ የንግድ ሥራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ለአቶ እንዳልካቸው ንጋቱ ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት የያዛቸውን እና ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን ፕሮጀክቶች እና የመያዣ ንብረቶቹን በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሻሻለው 216/92 እና 1147/2011 መሰረት ባሉበት ሁኔታ በድርድር ሽያጭ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
ተበዳሪው/የመያዣ ሰጪው/ ስም |
የሚሸጠው ንብረትና የሚገኝበት ቦታ |
የድርድሩ መነሻ ዋጋ |
ደረጃ
|
ድርድር የሚካሄድበት ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት |
|
1 |
ኬኛ ጠቅላላ የንግድ ሥራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት በአርሲ ዞን ዶዶታ ወረዳ፣ አዋሽ ብሾላ ቀበሌ ውስጥ 1 ሄክታር ይዞታ ላይ ያረፉ ግንባታዎች፣ የእንሰሳ (በግ/ፍያል) ማረጃ ማሽኖች፣ጀኔሬተር እና አንድ ባለ ማቀዝቀዣ ዩዲ ኒሳን ተሽከርካሪ |
44,999,333.61
|
2ኛ |
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መ/ቤት ነሃሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከ4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
|
2 |
እንዳልካቸው ንጋቱ |
በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት በምስራቅ ሽዋ ዞን ሉሜ ወረዳ፣ ጆጎ ጉዴዶ ቀበሌ ውስጥ 6000 ካ.ሜ ይዞታ ላይ ያረፉ ግንባታዎች፣ የወተት ማቀነባበሪያ መሽኖች እና 6 (ስድስት) ተሽከርካሪዎች |
46,286,021,48
|
2ኛ
|
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መ/ቤት ነሃሴ 13 ቀን 2018 ከ4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
ማሳሰቢያ
- ተደራዳሪዎች የድርድሩን መነሻ ዋጋ 25% (አስር በመቶ) የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ብቻ በማስያዝ መደራደር ይችላሉ።
- ተደራዳሪዎች የሚገዙትን ንብረት፤ የሚገዙበትን ዋጋ፤ ስምና አድራሻ በመጥቀስ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በማያያዝ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተ.ቁ 1 እስከ ነሃሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ለተ.ቁ 2 እስከ ነሃሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።
- ተደራዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መውሰድ ይችላሉ።
- ንብረቱን በብድር መግዛት የሚፈልግ ተደራዳሪ የባንኩን የብድር መስፈርት ማሟላትና ንብረቱን የሚገዙበት ዋጋ፣ ስለ ቀሪው የንብረት ዋጋ አከፋፈል ሁኔታ፣ ለቀሪው የንብረት ዋጋ አከፋፈል ከሚገዙት ንብረት በተጨማሪ የሚያቀርቡት የመያዣ ዓይነት፣ ግምትና የሚገኝበት ቦታ በመጥቀስ በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርበታል።
- አሸናፊው ያስያዘውን ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ሲታሰብለት ለተሸነፉ ተደራዳሪዎች ያስያዙትን ሲ.ፒ.ኦ ተመላሽ ይደረጋል።
- የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው የፕሮጀክቱ ንብረቶች ካሉ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል።
- የድርድሩ አሸናፊ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ድርድሩን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መስሪያ ቤት በአካል በመቅረብ ማነጋገር እና ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላሉ።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 022-211-66-87 ላይ መደወል ይቻላሉ።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪከት
Tender details
- Deadline: 2026-07-19
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Bid bond: 25%
- Published: Jul 12, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.