የቡራዩ መካነ እየሱስ ቤተክርስትያን ማምለክያ አደራሽ የውስጥ የጣውላ ኮርኒስ እና የከፊል ግድግዳ ሽፋን (cladding) ለማሠራት በዘርፉ በተሰማሩ ባለሙያ ወይም ድርጅት አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

Description

የጣውላ ኮርኒስ እና ተያያዥ ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ

የቡራዩ መካነ እየሱስ ቤተክርስትያን ማምለክያ አደራሽ የውስጥ የጣውላ ኮርኒስ እና የከፊል ግድግዳ ሽፋን (cladding) ለማሠራት በዘርፉ በተሰማሩ ባለሙያ ወይም ድርጅት ከታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

1. ተጫራች የቫት ተመዝጋቢ ሆኖ የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ክሊራንስ ማቅረብ . የሚችል፤

2. ተጫራች ተመሳሳይ የሆነ (የእንጨት ኮርኒስ እና የግድግዳ ሽፋን) ሥራ ቢያንስ አንድ ሠርቶ ያጠናቀቀ እና ለዚሁ ከአሰሪው የማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤

3. ተጫራች በእንጨት ሥራ ወይም የቤት ውስጥ ግንባታ ጨራሽነት እውቅና እንዳለው ከሚመለከተው የመንግስት አካል የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ያለው፤

4. ተጫራች የጣውላ ኮርኒስ እና የግድግዳ ሽፋን (cladding) የሚሰራበትን ጣውላ በሚፈለገው ስፋት፤ ውፍረት እና ቅርፅ ለማዘጋጀት እና ለመግጥም የሚያስችል መለስተኛ የእንጨት ስራ ማሽኖች፤ የተለያዩ የእጅ መሳርያዎችን እና አስፈላግ የሆኑ ዕቃዎችን ( መሳርያዎችን) ማቅረብና ማሟላት የሚችል፤

5. ተጫራች ጠቅላላ ከሚያቀርበው ዋጋ 2 በመቶ በ'CPO'' ወይም የባንክ ዋስትና (unconditional bank Guarantee) የጨረታ ማስከበርያ ከታወቀ ባንክ ለ 148 ቀን ማቅረብ የሚችል፤

6. ተጫራች ካሸነፈ ለሥራ አፈፃፀም ዋስትና የሚሆን ከታወቀ ባንክ ከሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋላይ 10 ፐርሰንት ለ 300 ቀን ዋስትና( performance bond unconditional bank Guarantee) ማቅረብ የሚችል

7. ይህ ማምለክያ አደራሽ የውስጥ የጣውላ ኮርኒስ እና የግድግዳ ሽፋን (cladding) የስራ ማስታወቅያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 የስራ ቀናት ብር 500 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ከቡራዩ ጤና ጣቢያ ጀርባ 100 ሜትር ገባ ብሎ ከሚገኘው ከቡራዩ መካነ እየሱስ ቤተክርስትያን አስተዳደር ቢሮ መግዛት ይችላሉ

8. የጫረታው ማስታወቅያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ተኛ ቀን ከቀኑ ስድስት ሠዓት ተዘግቶ በዝያው ዕለት ከቀኑ በ8፡00(ስምንት ሰዓት) ላይ ጨረታው ይከፈታል። ሃያ ሁለተኛ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተዘግቶ ይከፈታል።

9. ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 18ተኛው ቀን የስራው ሁኔታ እና አለካክ(ልኬት) ለተጫራቾች ገለፃ ስለሚድረግ ሁሉም ተጫራቾች እንዲሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን

10. የስራው ማጠናቀቅያ እና ማስረከብያ ጊዜ ውሉ ከተፈረመ ቀን ጀምሮ ባሉት 120 ( አንድ መቶ ሃያ ) ተከታታይ (ካሌንደር) ቀን ይሆናል

11. የጨረታው ቆይታ (Bid validity period) 45 (አርባ አምስት) ቀን ይሆናል።

ከላይ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ባለሙያ ወይም ድርጅት የቡራዩ መካኔ እየሱስ በተክርሰትያን ቡራዩ ጤና ጣቢያ ጀርባ በሚገኘው የቤተክርስቲያንዋ አስተዳደር ቢሮ በአካል ቀርቦ ያለውን መረጃ የማይመለሰ አንድ ኮፒ ( ንግድ ፍቃድ፣ ቫት፤ ቲንቁጥር፤ ክሊራንስ እና የብቃት ማረጋገጫ) በመያዝ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 21 ቀን ውስጥ ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ። ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፍል በማንኛውም ጊዜ የመሰረዝ የቤተክርስትያንቷ መብት በሕግ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡ 09 11 34 51 27 / 09 44 80 66 76 / 09 17 69 72 33 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

መካነ እየሱስ ማዕ/ኢት ሲኖዲስ የቡራዩ ገፈርሳ ሰበካ ቡራዩ ማ/ም


Tender details

  • Deadline: 2026-08-07
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታው ማስታወቅያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ተኛ ቀን ከቀኑ 6፡00 (ስድስት ሠዓት)
  • Bid opening: 2026-08-07 14:00
  • Bid opening (note): የጨረታው ማስታወቅያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ተኛ ቀን ከቀኑ በ8፡00(ስምንት ሰዓት)
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: የአት.ወ.ቤ.ክ.መካነ ኢየሱስ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሲኖዶስ የቡራዩ ማህበር ምዕመናን
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Jul 14, 2026
  • Posted at: 2026-07-14T08:11:14.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders