የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለሁለት አመት በሚቆይ የማዕቀፍ ስምምነት የጥበቃ አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል
Description
የጥበቃ አገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፦ NEBE/NCB/01/2019
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለሁለት አመት በሚቆይ የማዕቀፍ ስምምነት የጥበቃ አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል።
1- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 200.00 (ብር ሁለት መቶ) በመክፈል ከቦርዱ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 107 የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
2- ተጫራቾች የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ፋይናንሽልና ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3- ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የግብር ክሊራንስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ድረገጽ በኢጅፒ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስጃቸውን እንዲሁም የተፈረመና ማህተም ያለው የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የተገባበት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
4- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቦርዱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው። ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
5 ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ45 ቀናት ነው።
6- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና የተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል ፊርማ መኖር ይገባዋል።
7- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበርያነት ብር 100,000.00 (ብር አንድ መቶ ሺህ) በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
8- ተጫራቾች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀነ 8፡00 ድረስ ቦርዱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
9- ጨረታው ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት በ8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦርዱ ግዥ ስራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 107 ይከፈታል።
10- በጨረታው መክፈቻ ዕለት የተጫራቾች አለመኖር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም።
11- ቦርዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12- ተጨማሪ ማብራርያ ካስፈለገ በአካል ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ ባለው ዋ/መ/ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻችን፡-ቦሌ ፍላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡-+251 11 515 3468
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
Tender details
- Deadline: 2026-07-27
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-07-27 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: National Election Board of Ethiopia
- Buyer address: ቦሌ ፍላሚንጎ ካፌ ገባ ብሎ
- Bid bond: 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: Jul 17, 2026
- Posted at: 2026-07-17T08:16:59.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.