የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተለያዩ ንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተቁ |
የተበዳሪው የመያዣ ሰጪው ስም |
የንብረት ፕሮጀክት አድራሻ |
የንብረት/ፕሮጀክት ዝርዝር |
የቦታ ስፋት
|
የጨረታ መነሻ ዋጋ(በብር) |
የጨረታ ሁኔታ |
የጨረታ ደረጃ |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
|
1
|
ኤም ዋይ ሹዝ ኤንድ ሌዜር ማኑፋቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማ
|
አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደብረ ብርሃን ከተማ 09 ቀበሌ
|
የጫማ እና የቆዳ ማምረቻ ፋብሪካ (በትግበራ ላይ ያለ) የህንፃ ግንባታዎች፣ ማሽነሪዎች እና የኤልክትሪክ ሥራዎች እና የክምች ዕቃዎች |
6.83 ሄክታር
|
ብር 457,236,714.80 (አራት መቶ ሃምሳ ሰባት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰላሳ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ አስራ አራት ብር ከሰማንያ ሳንቲም) |
ዝግ
|
አንደኛ
|
ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሰዓት
|
|
2
|
አቶ ግርማ አፈወርቅ መድምም
|
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ ስ/ላ/ክ/ ከተማ ወረዳ 08
|
ጋቴፕሮ ቆርቆሮ ፋብሪካ፤የህንፃ ግንባታዎች፤ የኤሌክትሪክ ሥራዎች፤ ማሽነሪዎች፤ ቁሳቁሶች፤ የቢሮ ዕቃዎችና መገልገያዎች፤ የጥሬ ዕቃና የምርት ከምችት |
1,678 ካሬ ሜትር |
122,600,997.28 (አንድ መቶ ሃያ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሜትር ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት ብር ከሃያ ስምንት ሳንቲም)
|
ልዩ ድርድር
|
ሁለተኛ
|
ነሐሴ 12 ቀን 208 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሰዓት
|
ማሳሰቢያ፤
1. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በፎርማቱ ላይ በመጥቀስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ሁለተኛ ታወር ምድር ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ ከሦስተኛው ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 11 እና ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ እንደየቅደምተከተላቸው ማስገባት ይችላሉ።
2.ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
3. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።
4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ በተመለከቱት ቀናት 4፡00 ሰዓት ላይ ተከፍቶ እስከ 6፡0 ሰዓት በባንኩ ዋናው መ/ቤት ይካሄዳል፡፡ህጋዊ ሰውነት ያላቸው አካላትን ወከሎ በጨረታው ለመሳተፍ የሚቀርብ ሰው የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ መተዳደሪያ ደንብ ከእነ ማሻሻያዎቹ (ካለ)፣ የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፍቃድ፣ ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን እና የተረጋገጠ የውክልና ስልጣን ሰነዶችን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
5. 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ከፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል።
6. አንዳንድ የድርጅቶቹ ንብረቶች የጉምሩከ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆኑ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም የሚፈለገውን ቀረጥ ታክስ ለመንግስት ለመከፈል ይገደዳል።
7. የጨረታው አሸናፊ የባንኩን የብድር መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ ከፊል ብድር ሊመቻችለት ይችላል፤ (ኤም ዋይ ሹዝ ኤንድ ሌዜር ማኑፋቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ብቻ።
8. የንብረቱ ስመ-ንብረት ለገዥው እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል:: ገዥው ጉዳዩን ተከታትሎ ያስፈፅማል።
9. ተጫራቾች ንብረቱን ለመጎበኘት ከፈለጉ አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በመያዝ ንብረቱን መጎበኘት ይችላሉ።
10. በጨረታው ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦንጎይንግ ኮንሰርን ፕሮጀከትስ እና አኳየርድ አሌትስ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-524 53-73/ 011 524 42 69 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።
11.ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
Tender details
- Deadline: 2026-08-18
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
- Published: Jul 19, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.