ቢ.ኤም የቤት ግንባታ እና ኪራይ አክሲዮን ማሕበር የአንድ ወለል የማጠናቀቂያ ስራ (4 floor)አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቢ.ኤም የቤት ግንባታ እና ኪራይ አክሲዮን ማሕበር በመርካቶ አካባቢ በተለምዶ አሜሪካ ግቢ እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ 3B+SB+G+14 ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሕንጻ እያስገነባ ይገኛል። በመሆኑም የአንድ ወለል የማጠናቀቂያ ስራ (4th floor) አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
የጨረታ ተወዳዳሪ ሥራ ተቋራጭ ሙሉ ሀላፊነት ወስዶ የሚሰራበት/Supply and Fix/ ወይም የሰው ኃይል፣ የእጅ መሳሪያ እና ማሽነሪ የሚያቀርብበት(labor Based Contract) ለማሰራት ግልጽ ጨረታ ባለሁለት ኢንቨሎፕ(ፖስታ) ጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
ከጨረታው ሰነድ ጋር፡-
- ደረጃቸው/Category GC-5 ወይም BC-5 እና ከዚያ በላይ ያላቸው፤
- በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ አግባብነት ያለው ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፤
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ሰርተፍኬት እና የቲን ቁጥር ማቅረብ አለባቸው፤
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ማስረጃ ከግብር ዕዳ ነጻ ስለመሆናቸው ክሊራንስ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ቢ.ኤም የቤት ግንባታ እና ኪራይ አክሲዮን ማሕበር ዋና መሥሪያ ቤት ቢሮ( ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ በሚገኘው ከኩርቱ ሕንጻ ፊት ለፊት ጊዜያዊ ፖሊስ ስቴሽን ጀርባ ባለው አሜሪካን ጊቢ ህንፃ 4ኛ ፎቅ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺ ብር) በቢ.ኤም የቤት ግንባታ እና ኪራይ አክሲዮን ማሕበር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000537291676 ገቢ ያደረጉበትን የባንክ ደረሰኝ ይዘው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነዱን መውሰድ/መግዛት/ ይችላሉ፤
- ከተሰጠው ስፔሲፊኬሽን ወይም የቴክኒክ ፍላጎት መግለጫ ውጪ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከውድድር ውጪ ይሆናሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው:: ይህ ካልሆነ የቀረበው ዋጋ ከነቫቱ እንደቀረበ ተደርጎ ይወሰዳል፤
- በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር የተገለጹ የግንባታ ሥራዎች የማቅረቢያ/ የማጠናቀቂያ ጊዜ በውል ስምምነት የሚገለጽ ሆኖ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፋቸውን የግንባታ ሥራዎች በተገለጸው ጊዜ የማስረከብ ግዴታ አለበት፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ በቢ.ኤም የቤት ግንባታ እና ኪራይ አክሲዮን ማሕበር ስም አዘጋጅተው ለብቻው በፖስታ በማሸግ ከኦሪጂናል ቴክኒካል ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች የማጠናቀቂያ ሥራውን ዝርዝር ቴክኒካል እና ፋይናንሺል ሰነድ በመለየት ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አባሪ አድርገው በተሰጠው ስፔሲፊኬሽን ላይ በመሙላትና የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በሁሉም ገጾች ላይ በማሳረፍ 1 (አንድ) ኦሪጂናል ቴክኒካል እና 1 (አንድ) ኦሪጂናል ፋይናንሺያል እያንዳንዱ በጠቅላላ 1 ኮፒ ፋይናንሺያል እና 1 ኮፒ ቴክኒካል አሜሪካን ጊቢ ኩርቱ ሕንጻ ፊት ለፊት ከጊዜያዊ ፖሊስ ስቴሽን ጀርባ አሜሪካን ጊቢ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የቢ.ኤም የቤት ግንባታ እና ኪራይ አክሲዮን ማሕበር ዋና መሥሪያ ቤት ቢሮ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በ 25/11/2018 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 - 4፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
- ጨረታው በ25/11/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ይከፈታል፤
- የጨረታው ውጤትም ቴክኒካል ተገምግሞ እንዳለቀ በደብዳቤ/በፋክስ/በስልክ እና በውስጥ ማስታወቂያ በማሳወቅ በመቀጠልም ፋይናንሺያል የሚከፈትበት ጊዜ የሚገለጽ ይሆናል፤
- ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና (ውል ማስከበሪያ) በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ያቀረቡት ዋጋ ቢያንስ ለ60 ቀናት ጸንቶ መቆየት ይኖርበታል፤
- ማንኛውም ተጫራች በውል ውስጥ የተካተቱትን ሕጎች ማክበር አለበት
- አክስዮን ማሕበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር +251 90 033 3414 /+251 90 993 1111 ደውሉ ማግኘት ይቻላል።
Tender details
- Deadline: 2026-08-01
- Publishing entity: B.M Housing Construction and Rental S.C.
- Bid bond: 100,000 ብር
- Bid document price: 1000.00 ብር
- Published: Jul 19, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.