የቃሊቲ ሀቢታት ሪል እስቴት የቤት ባለቤትና የነዋሪዎች ኃ/የተ/የህ/ስ ማህበር አድራሻው አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 7 ብሎክ 38 በተለምዶ ቃሊቲ በርታ ሪል እስቴት ግቢ በመባል የሚታወቀው ለተለያዩ ሥራዎች ተቋራጭ ድርጅት ለመምረጥ የሚያስችል የሥራ ይዘትና የዋጋ ተመን ያለበት የጨረታ ሰነድ እንዲቀርብለት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የቃሊቲ ሀቢታት ሪል እስቴት የቤት ባለቤትና የነዋሪዎች ኃ/የተ/የህ/ስ ማህበር አድራሻው አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 7 ብሎክ 38 በተለምዶ ቃሊቲ በርታ ሪል እስቴት ግቢ በመባል የሚታወቀው ለሚከተሉት ሥራዎች ተቋራጭ ድርጅት ለመምረጥ የሚያስችል የሥራ ይዘትና የዋጋ ተመን ያለበት የጨረታ ሰነድ እንዲቀርብለት ይፈልጋል::

1. ርዝመቱ ዋና የግቢ ዙሪያ አጥር በአይነቱ የኮንክሪት መደብ ኖሮት ቁመት 2.50 ሜትር በሆነ የብረት ቋሚዎችና ማገሮች የሚሰራ ሆኖ በሜሽ ዋየር የሚሸፍንና ከላይ ላለ ሾክ አደገኛ ሽቦ የሚዘረጋበት ይሆናል::

2. የውስጥ መንገዶች አሁን ያለውን የአስፋልት መንገድ ለመጠገንና ለማጠናከር እንዲሁም ቀሪውን የኮብል ድንግጋይ መንገድ ወደ አስፋልት ደረጃ ለማሳደግ ሲሆን የሚሻሻለው አስፋልት መንገድ ርዝመት 1540 ሜትር ስፋት 7 ሜትር ሲሆን የኮብሉ መንገድ ርዝመት 1944 ሜትር ስፋት 7 ሜትር ይሆናል:: አስፋልቱ ባለ 4 ሴ.ሜ ውፍረት ያለው ኮንክሪት አስፋልት ሆኖ አንድ ወጥ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ይፈልጋል::

ይህንን ስራ ለመስራት ዝግጅቱና ወቅታዊ የሥራ ፈቃድ ያላችሁ ድርጅቶች የዋጋ ተመንና ሥራው ከተጀመረ በኋላ በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ እንደሚቻል ጭምር ተገልጾ እንዲቀርብ እናሳስባለን::

ለበለጠ መረጃ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ - አርብ ከጠዋቱ 2፡30 - 6፡30 እንዲሁም 7፡30 – 11፡00
በስልክ ቁጥር፡-0114-71-73-14 መረጃ ማግኘት ይችላሉ::
የቃሊቲ ሀቢታት ሪል እስቴት የቤት ባለቤቶችና የነዋሪዎች  ኃ/የተ/የህ/ስ/ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-07-31
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰአት አልተገለፀም
  • Bid opening: 2026-07-31 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰአት አልተገለፀም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kality Habitat Real Estate Home Owners and Residents Plc
  • Published: Jul 19, 2026
  • Posted at: 2026-07-20T13:41:27.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders