የጅማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በጅማ ከተማ መስተዳደር ስር ለሚገኙ መስሪያ ቤቶች እና ለጅማ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጅማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በጅማ ከተማ መስተዳደር ስር ለሚገኙ መስሪያ ቤቶች እና ለጅማ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውሉ፡-
1. የጽህፈት መሳሪያ፤
2. የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ፤
3. የጽዳት መሳሪያ፣
4. የተለያዩ የመኪና እና የማሽነሪ ጎማዎችን፤
5. የደምብ ልብሶች
6. የተለያዩ ሞተር ሳይክሎች እና
7. የቢሮ እቃዎችን (Furniture) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡-
ስለሆነም ፡
1. በተጠቀሱት የስራ አይነቶች ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን(2018) ግብር የከፈሉና ንግድ ፈቃዳቸውን ለ2019 የስራ ዘመን ያሳደሱ እና የታደሰውን ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
3. TIN እና VAT ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና TAX clearance ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከጅማ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ የማይመለስ ብር 1700 (አንድ ሺህ ሰባት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ተከታታይ በመንግስት የስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
5. ለጨረታው ማስከበሪያ 100,000 (መቶ ሺህ) ብር ሲፒኦ በጅማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም አሰርተው ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው (ለእያንዳንዱ ጨረታ)።
6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻልና ቴክኒካሉን ኦርጂናሉንና ኮፒውን በመለየት በኢንቨሎፕ ታሽጎ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀናት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።
7. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ 15 የስራ ቀን ሲሆን ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የመንግስት የስራ ቀን 8፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን 9፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
8. በተባለው ቀንና ሰዓት ያልመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ሳይከፈት ለባለቤቱ ተመላሽ ይሆናል።
9. የጨረታው አሸናፊ ንብረቱን በራሱ ትራንስፖርት በጅማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በተባለበት ቦታ ገቢ አድርጎ ገንዘቡን ይቀበላል።
10. በዚህ ማስታወቂያ የተጠቀሱት መስፈርቶች በሰነዱ ላይ ከተጠቀሱት መስፈርቶች ጋር የመጀመሪያ ዙር ቴክኒካል ግምገማ ነጥቦች ይሆናሉ።
11. ጽህፈት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
የጅማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 አባ ጂፋር አደባባይ ጅማ ከተማ መስተዳደር ቅጥር ግቢ
Jimma city Administration yard, Finance Office Building, Ground Floor ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0472114408 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የጅማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-06
- Bid closing time: 14:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ 15 የስራ ቀን ሲሆን ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የመንግስት የስራ ቀን 8፡30
- Bid opening: 2026-08-06 15:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ 15 የስራ ቀን ሲሆን ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የመንግስት የስራ ቀን 9፡00
- Region: Oromia
- Publishing entity: Jimma City Finance Office
- Bid bond: ለእያንዳንዱ ጨረታ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 1700 (አንድ ሺህ ሰባት መቶ ብር)
- Published: Jul 21, 2026
- Posted at: 2026-07-21T07:39:52.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.