የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ዙር ኮሌጁ ለሥልጠና አገልግሎት እና ለቢሮ አገልግሎት የሚያገለግሉ ቋሚ የአይሲቲ ግብዓት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
|
ተ/ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
|
ሎት 1 |
ቋሚ የተለያዩ አይሲቲ ግብዓት |
100,000.00 |
ለ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ዙር ኮሌጁ ለሥልጠና አገልግሎት እና ለቢሮ አገልግሎት የሚያገለግሉ ቋሚ የአይሲቲ ግብዓት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት ማሟላት አለባቸው።
1. በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በአቅራቢነት የተመዘገቡ ስለመሆኑ የምዝገባ ምስክር ወረቀትና የታከስ ሰርተፊኬት ያላቸው።
2. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ከመንግሥት ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከCPO ውጭ እንደማንቀበል እናሳስባለን።
5. ተጫራቾች በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ CPOውን ቴክኒካል ኦርጅናል ውስጥ በመክተት በደንብ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ኤንቨሎፑ ላይ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ፤ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ ተብሎ መገለፅ ይኖርበታል፡፡ ስለዚህ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች ለተጫረቱበት ግብዓት ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል ናሙና ላላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውጭ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በ4፡30 ጨረታው ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡-
በጨረታው ተሣታፊ የሚሆነው ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራች ብቻ መሆኑን እናሣውቃለን።
ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር: 0114 173 226 / 0118 495 158 / 0114 343 336 / 0111 417 3226/
የመ/ቤቱ አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ደብረ ዘይት መንገድ መውጫ ፍተሻ ሳይደርስ የሺ ቶታል አለፍ ብሎ ወደ ግራ በሚወስደው መንገድ 800 ሜትር ገባ ብሎ ነው።
የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-07-31
- Publishing entity: Akaki Poly Technic College
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Jul 20, 2026
- Posted at: 2026-07-21T07:43:26+00:00
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.