ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

1. የተለያዩ፣

  • የደንብ ልብሶች፣
  • አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
  • የፅህፈት መሳሪያዎች፣
  • የፅዳት ዕቃዎች፣
  • ግርግዳ ላይ የሚታሰር የእንጨት ፋይል መደርደሪያ፣
  • የአይሲቲ ዕቃዎች፣
  • የቢሮ ፈርኒቸሮች ጥገና፣
  • የአይሲቲ ዕቃዎች ጥገና፣
  • የመስተንግዶ አገልግሎት፣
  • የህትመት አገልግሎት የዲኮር እና የዲጄ አገልግሎት፣
  • የጉልበት ስራ አገልግሎት፣
  • የትራንስፖርት ኪራይ አገልግሎት፣
  • የጀነሬተር ጥገና እና
  • የብረታብረት ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

 ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

1.1.1. ተጫራቾች በመንግስት ግዢ በዕቃ አቅራቢነት ውስጥ የተመዘገቡ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

1.1.2. ተጫራቾች እኛ ከሰጠነው የጨረታ ሰነድ የዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ውጪ ሞልቶ የሚያቀርብ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም።

1.1.3. ተጫራቾች ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ሠነድ /ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

1.1.4. ተጫራቾች ከስር ከተጠቀሱት ሎቶች ውጪ ለእያንዳንዱ ሎቶች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አጠቃላይ ያቀረቡትን ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

1.1.5. ለመስተንግዶ አገልግሎት፣ ለህትመት አገልግሎት፣ለትራንስፖርት አገልግሎት፣ ለጥገና አገልግሎት፣ ለጉልበት ስራ አገልግሎት፣ ለዲጄ አገልግሎት እና ለብረታብረት ስራ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

1.1.6. ለግርግዳ ፋይል መደርደሪያ ስራ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል

1.1.7. አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የውሉን 10%ማስያዝ ይኖርበታል

1.1.8. ገዢው መስሪያ ቤት በጨረታው ወቅት 25% ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል።

1.1.9. በተጨማሪም ገዢው ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከተዋዋለበት ቀን ጀምሮ 20% እስከ 6 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ሊጨምር ይችላል።

ተጫራቾች በተሰጣቸው የንግድ ዘርፍ ብቻ መሳተፍ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

1.1.11. ተጫራቾች ናሙናቸውን ከጨረታ መክፈቻው በፊት ማሥገባት ይኖርባቸዋል።

1.1.12. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።

1.1.13. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል በቂ/ክ/ከ/የወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት ውስጥ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

1.1.14. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

1.1.15. ተጫራቾች ለጨረታው ያቀረቡትን ዋጋ የሚቆይበትን ጊዜ ቢያንስ ለ 60 ቀን መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል።

1.1.16. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን ተጫራቾች ወይም ህግዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቂ/ክ/ከ/የወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል።

1.1.17. የወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡-

በአ/አ/ከ/አስ/የመንግስት ግዢ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 17/2002 አንቀፅ 17 ንዑስ 2 እና የግዢ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 3/2002 አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀፅ 20.5 በተደነገገው መሰረት ለጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የጨረታ ሰነድ በነፃ የምንሰጠው በሃገር ውስጥ ምርት ማምረት ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ብቻ መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-515-8838

አድራሻ፡- ብሄራዊ ከበድሉ ህንጻ በስተጀርባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

አዲስ አበባ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-03
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-04 10:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kirkos Sub-City Woreda 07 Finance Bureau
  • Buyer address: ከብሄራዊ ከበድሉ ህንጻ በስተጀርባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Jul 23, 2026
  • Posted at: 2026-07-23T08:11:55.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders