የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ጉ/ክ/ከ/ወ/3/ፋይናንስ ጽ/ቤት 001/2019 ዓ.ም
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጻም ይፈልጋል።
- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ
- ሎት 2. የጽዳት ዕቃ
- ሎት 3. የደንብ ልብስ
- ሎት 4. የደንብ ልብስ ስፌት
- ሎት 5. ህትመት አገልግሎት
- ሎት 6.የትራንስፖርት አገልገሎት
- ሎት 7. ቋሚ እቃ
- ሎት 8. የካፌ አገልግሎትና መስተንግዶ ገዥ
- ሎት 9 የኮምፒውተር፤- ፕሪንተር እና ፎቶኮፒ ፕገና፤ሞንታርቦ ጥገና
- ሎት10 የህንፃ እቃዎችና ልዩ ልዩ እቃዎች
በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያማሱ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
1. ሚወዳደሩበት የንግድ ዘርፍ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግስት ዕቃ ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
2. የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ሎት 1የጽህፈት መሳሪያ 50,000 ብር /ሀምሳ ሺህ ብር/ሎት 2.የጽዳት ዕቃ 50,000 ብር /ሀምሳ ሺህ ብር/፤ ሎት3, የደንብ ልብስ 50,000 ብር (ሀምሳ ሺህ ብር) /ሎት 4.የደንብ ልብስ ስፌት 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ 5.ህትመት 10,000 ብር / አስር ሺህ ብር/፤ሎት6. የትራንስፖርት አገልግሎት15,000/፤አስራ አምስት ሺህ ብር / ሎት 7 ቋሚ እቃ 10,000 (አስር ሺህ ብር) ሎት8. የካፌ አገልግሎት መስተንግዶ 40,320 (አርባ ሺህ ሶስት መቶ ሃያ ብር) ሎት9. የኮምፒውተር፤ ፕሪንተር፤ ፎቶ ኮፒ ጥገና 4,000 (አራት ሺህ ብር ) ሎት 10) የህንፃ እቃዎችና ልዩ ልዩ እቃዎች 5,000(አምስት ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ በጉ/ክ/ከ/ ፋይናንስ ጽ/ቤት በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል።
3. ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ከመ/ቤታችን ጋር የውል ማስከበሪያ ላሸነፉባቸው እቃዎች የጠቅላላ ዋጋውን (10%) በባንክ በተመሰከረ / cpo / ማቅረብ ይጠበቅባችኋል። ይህ ባይሆን ግን በጨረታ ያስያዙት ሲፒኦ በቀጥታ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
4. የሚያቀርቡት የዕቃው ዋጋ በሁለት ፖስታዎች ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በመምጣት ለዚሁ በተዘገጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
5 ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን 04፡30 በወረዳው አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል የመክፈቻው ቀን በዓል ወይም እረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
6. የጨረታው ዝርዝር የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 150 ብር / አንድ መቶ ሃምሳ ብር በመክፈል ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 መውሰድ ይችላሉ።
7. ተጫራቾች ለመወዳደር በመረጡት ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በወረዳው ጽ/ቤት ማቅረብ አለባቸው።
8. የሚቀርበው የእያንዳንዱ ዕቃ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል።
9. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የአቅራቢነት ማስረጃ ኮፒ የሚታይ መሆን አለበት።
10. አቅራቢ ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ንብረት ክፍል መድረስ ይኖርበታል።
11. አስተዳደሩ ባወጣው ጨረታ ላይ ከውል በፊት የእቃው ብዛት 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል እንዲሁም ከውል በኋላ ደግሞ 25 የዋጋውን መጨመር መቀነስ ይችላል። በጨረታ መወዳደሪያ የሚቀርብ ዋጋ ለስድስት ወር ፀንቶ ይቆያል።
12. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ማብራሪያ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 011 122-2600 መደወል ይቻላል።
ማሳሰቢያ፡- ለጥቃቅን እና አነስተኛ ተጫራቾች ቅድሚያ እንሰጣለን መተጨማሪም መወዳደር የሚችሉት አምራች በሆኑበት የንግድ ዘርፍ ብቻ ነው።
አድራሻ፡- ከመነን ሽሮሜዳ በሚወስደው መንገድ ፀሃይ ጮራ ት/ቤት ፊት ስፌት
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-04
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-05 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 04፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Gulele Sub City Woreda 3 Finance Office
- Buyer address: ከመነን ሽሮ ሜዳ በሚወስደው መንገድ ፀሐይ ጮራ ት/ቤት ፊት ለፊት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/
- Published: Jul 24, 2026
- Posted at: 2026-07-24T08:08:53.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.