Addis Ababa
አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ. የስብሰባ አዳራሽ ወንበሮች የግልጽ የጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማከራየት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 09/2018
አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 እና በማሻሻያ አዋጅ 807/2005 መሰረት የካፒታል እቃ ፋይናንስ ስርዓት ለማቅረብ የተቋቋመ እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የስራ ፈቃድ የተሰጠው የፋይናንስ ተቋም ሲሆን በአራዳ ክ/ከተማ ከጊወርጊስ ቤተክርስቲያን ወደ 6 ኪሎ በሚወስደው መንገድ ድንበሬ መታሰቢያ ህንጻ ጎን የሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት ህንጻ ውስጥ 1 ፎቅ፣ 9ኛ ፎቅ የGYM ፣ ቦሌ ክ/ከተማ ቡልቡላ ሳይት እና ለሚኩራ ክ/ከተማ ሰሚት ሳይት የሚገኘው 40/60 የጋራ መኖሪያ ኪራይና የዋና መስሪያ ቤት የስብሰባ አዳራሽ ወንበሮች የግልጽ የጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማከራየት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ጋብዘናል።
1. ተጫራቾች ተወዳድረው ባሸነፉበት ቤት ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ለማውጣት፣ ቤቱን ተከትሎ የተጠቀሙበትን የውሃ እና የመብራት ፍጆታ ለመክፈል ፍቃደኛ መሆን አለባቸው።
2. አዳራሽ ወንበሮች ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን በዘመኑ የታደስ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ሚችሉ እና በአቀራቢወች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የኩባንያው አዲስ ሕንፃ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ፣9ኛ ፎቅ ለ GYM አገልግሎት፣ 40/60 ቤቶች ኪራይ 5000 (አምስት ሺህ ብር) እና የዋና መሥሪያ ቤት የስብሰባ አዳራሽ ወንበሮች 50000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 5/2018 ዓ.ም የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ወደ 6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ መታሰቢያ ሕንፃ ጎን በሚገኘው አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ ኢማ ዋና መሥሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ፣ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ፋይናንሽያል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ እስከ ነሐሴ 5/2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው በቀን ነሐሴ 5/2018 ዓ.ም በ4፡00 ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ 4ኛ ፎቅ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል።
7. ኩባንያው ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ - ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ወደ 6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ መታሰቢያ ህንጻ ጎን፣
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር +251112179962 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-08-11
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-08-11 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Capital Goods Finance Business S.C
- Buyer address: Arat Kilo next to Tourist hotel Ethiopian Post service organization building 3rd floor, procurement administration directorate office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Jul 25, 2026)
- Posted at: 2026-07-25T07:42:43.000Z