Finishing and renovation works

በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት ስር የሚገኘው ለሰላም በር ቅ/አ/አ እና የመ/ደ/ት/ ቤት በ2019 በጀት ዓመት በውስጥ ገቢና በመደበኛ በጀት የተለያዩ የጥገና ሥራዎችን አወዳድሮ በአሸናፊው ድርጅት ማሠራት ይፈልጋል

Description

የጥገና ሥራዎች ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ መመሪያ መ.ቁ.01/19

በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት ስር የሚገኘው ለሰላም በር ቅ/አ/አ እና የመ/ደ/ት/ ቤት በ2019 በጀት ዓመት በውስጥ ገቢና በመደበኛ በጀት የተለያዩ የጥገና ሥራዎችን ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሕጋዊ ሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ በአሸናፊው ድርጅት ማሠራት ይፈልጋል።

ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሠ የንግድ ፍቃድ መሆኑን የሚገልፅ አግባብነት ያለው ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል በተጨማሪ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ሕጋዊ ሰነዶች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

1. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ በሰላም በር ቅ/አ/አ እና መ/ደ/ት/ቤት ከፍያና ሂሳብ አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት (ቢሮ ቁጥር 6 ) በመቅረብ የማይመለስ 300 ብር / ሦስት መቶ ብር / ከፍለው የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል የጨረታ መስፈርቱን ያሟሉ ተጫራቾች በእለቱም ባይገኙም ፖስታቸው ይከፈታል።

2. ተጫራቾች ከጨረታ ሠነዳቸው ጋር ተዛማጅና ተያያዥነት ባላቸው ሥራዎች ከመንግሥት ተቋማት ቢያንስ አራት ዓመት የሠሯቸው የመልካም አፈፃፀም የምስክር ወረቀት (ደብዳቤ) አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የሚያቀርቡት የሥራ አይነት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ የሌለበት፣ ሥልጣን ባለው አካል የተፈረመባቸው የተሟላ አድራሻቸውን የሚገልጽና ሕጋዊ ማህተም ያረፈበት ሊሆን ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 10,000 በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ በት/ቤቱ ስም በማሠራት ከጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሠዓት በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ የዋጋ ለውጥም ሆነ ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም በተወዳደሩት ዋጋ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በ5 ቀናት ውስጥ ቀርበው የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ በት/ቤቱ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለጸበት በ5 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል ካልተዋዋለ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል።

7. አሸናፊ ተጫራች በስፔስፍኬሸኑ መሠረት ሥራው የሚጠቀምባቸው ማቴሪያሎች የጥራት ደረጃ ት/ቤቱ በመደበው ባለሙያ የጥራት ደረጃቸው ሲረጋገጥ ብቻ ነው ወደ ሥራው መግባት የሚችሉት

8. ት/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች ከመረጠ በኋላ በሚያሠራው ግንባታ እና እድሳት ሥራዎች ላይ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 30% የመቀነስም እንዲሁም የመጨመርም መብቱ የተጠበቀ ነው።

9. ተጫራቾች የግንባታ ሂደቱን የሚያከናውኑት ት/ቤቱ በሚያቀርበው ዲዛይን መሠረት ብቻ ነው።

10. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. በጨረታው ሰነድ ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮች ካሉ በአካል በመቅረብ ሠላም በር ቅድመ አንደኛ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥ ቢሮ መጠየቅ ይችላሉ።

12. ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ሲሞላ 15% ቫትን በመጨመር ይሆናል፡፡ 15% ቫትን ያላካተተ ተጫራች ለውድድር አይቀርብም።

13. ተጫራቾች የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፅም ቃል የሚገቡበትን ፎርማትን በመሙላት የተጫራቹን ድርጅት ፈርማና ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።

አድራሻ ፡- በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ሉካንዳ ታክሲ ማዞሪያ ወደ ፌደራል ፖሊስ ማሠልጠኛ ተቋም በሚወስደው አስፓልት በስተቀኝ በኩል ሰዋሰው ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ጎን

ስልክ ቁጥር 0112 739 095 / 0112 739 030

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ሠላም በር ቅድመ አንደኛ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-06
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-06 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ሰላም በር ቅድመ አንደኛ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jul 25, 2026)
  • Posted at: 2026-07-25T08:16:35.000Z
← Back to all tenders