Addis Ababa
ዘ ብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ (The Brooke Hospital for Animals) የተለያዩ የግንባታ እና ጥገና ስራዎችን ለማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ዘ ብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ (The Brooke Hospital for Animals) በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በቁጥር 0883 የተመዘገበ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረሰናይ ድርጅት ሲሆን ከተመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ ዋና ቢሮውን አዲስ አበባ በማድረግ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። የድርጅቱ አላማ የጋማ እንስሳትን ደህንነትና ጤንነት ማሻሻል እና በእነዚህ የጋማ እንስሳት ጉልበት ኑሯቸውን የመሰረቱ የማህበረሰብ ክፍሎችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ሲሆን ይህንንም ለመተግበር ከመንግስት የእንስሳት እና የግብርና ተቋማት ጋር በትብብር ይሠራል።
ድርጅታችን በዚህ ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ስራዎችን ለመስራት ይፈልጋል። ይህንንም ለማከናወን ድርጅታችን ብሩከ ኢትዮጵያ ብቁ እና መስፈርቶችን የሚያሟሉ ደረጃ ስድስት ጠቅላላ/ህንጻ ስራ ተቋራጭ (GC/BC Six and above) ለእንሰሳት ጤና ኬላ ግንባታ ስራዎች እና ደረጃ ሰባት ጠቅላላ/ህንጻ ስራ ተቋራጭ (GC/BC Seven and above) ለነገሌ አርሲ የእንሰሳት ክሊኒክ ጥገና እና ለሀላባ ሼድ ስራ የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎኘ በማቅረብ እንድትወዳዳሩ ይጋብዛል።
|
የጨረታ ቁጥር |
የፕሮጀክቱ ስም |
ዞን/ወረዳ/ቀበሌ |
የስራው ዓይነት |
|
|
1-የእንሰሳት ጤና ኬላ ግንባታ |
||||
|
ሀ-በኦሮሚያ ክልል |
||||
|
B-ETH/007/2026 |
Mara Aleme Animal Health Post |
Jimma /Dedo/Mara Aleme |
Main block, dry latrine, guard house, cattle crush, shade, water trough, roto with tanker fence etc. |
|
|
B-ETH/008/2026 |
Anano Animal Health Post |
East showa /Batu/Anano shasho |
Main block, dry latrine, guard house, cattle crush, shade, water trough, roto with tanker fence etc. |
|
|
ለ-በአማራ ክልል |
||||
|
B-ETH/009/2026 |
Boru Meda Animal Health Post |
South Wollo/Desse Town/Boru Meda |
Main block, dry latrine, guard house, cattle crush, shade, water trough, roto with tanker fence etc. |
|
|
B-ETH/010/2026 |
Kara Gutu Animal Health Post |
South wollo/Desse town/Borekena |
Main block, dry latrine, guard house, cattle crush, shade, water trough, roto with tanker fence etc.
|
|
|
B-ETH/011/2026 |
Metene Animal Health Post |
South Wollo/Kombolcha Town/Metene |
Main block, dry latrine, guard house, cattle crush, shade, water trough, roto with tanker fence etc. |
|
|
B-ETH/012/2026 |
Biraro Animal Health Post |
South Wollo/Kombolcha Town/Ras Ageze |
Main block, dry latrine, guard house, cattle crush, shade, water trough, roto with tanker fence etc. |
|
|
ሐ- በሲዳማ ክልል |
||||
|
B-ETH/013/2026 |
Teremesa Animal Health Post |
North Sidama /Shebedino/ Taremesa
|
Main block, dry latrine, guard house, cattle crush, shade, water trough, roto with tanker fence etc. |
|
|
2-የግንባታ እና ጥገና ስራ |
||||
|
ሀ-ኦሮሚያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል |
||||
|
B-ETH/014/2026 |
Negele Arsi Animal Clinic Renovation Work and Halaba Farreiry Shade Construction |
Negele Arsi/Negele Arsi Town And Halaba/Halaba Kulito Town |
Renovation of Negele Arsi Animal Clinic Blocks and Farreiry Shade Construction at Halaba |
|
1) ተጫራቾች ህጋዊና የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያላቸመሆን አለባቸው። /የጨረታ ሰነድ ስትገዙ ማቅረብ ይጠበቅባቹሃል።
2) ተጫራቾች የተሟላ የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የቤት ቁጥር 797 ከሚገኘው የድርጅታችን ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ ብር) በመክፈል ከጠዋቱ 2:30 አስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ በአካል በመገኘት መግዛት ይችላሉ።
3) ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው የጨረታ ዋጋ 2% በሲፒኦ መልክ ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ሲፒኦው የጨረታ ኤንቨሎኘ ውስጥ ለብቻ ታሽጎ መቅረብ አለበት። የቀረበው ሲፒኦ ከሂሳብ ስሌት ማስተካከያ በኋላ ለሚመጣው ጠቅላላ ዋጋ የ2ቱን ከ20% በታች ከሆነ ተጫራቹ ከውድድር ውጪ ይደረጋል።
4) ተጫራቹ አሸናፊ ከሆነ ለቅድመ ክፍያ የሚሆን የሁኔታዎች ያልተወሰነ /Unconditional Bank Guarantee/ የባንክ ዋስትና 30% ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል።
5) ተጫራቾች በሰም የታሸገውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ከላይ በተ.ቁ. 2 በተጠቀሰው አድራሻ በሚገኘው የብሩክ ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በ15ኛው ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ሲሆን። የጨረታ ማቅረቢያው 15ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀናት ከዋለ የጨረታ መዝጊያው ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይሆናል። ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውጭ የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
6) ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋበት ቀን በተ.ቁ. 5 የተመለከተው ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ይከፈታል።
7) ማንኛውም ተጫራች ከአንድ ጨረታ በላይ መሳተፍ አይቻልም።
8) ድርጅቱ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የጨረታ መክፈቻውን ቀን የማራዘም ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ እንዲሁም ቀደም ብሎ በድርጅቱ ሥራዎች ላይ ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸውን የጨረታ ተወዳዳሪዎች ከጨረታው እንዳይሳተፉ ማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9) ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-661-0069/ 011-662-1885 በመደወል ወይም በኢሜይል [email protected] አድራሻችን መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻችን፣ 22 ማዞሪያ ተሸአብ ህንፃ ፊት ለፊት ከቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል በጀርባ ባለው መንገድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ወደ 24 በሚወስደው መንገድ ላይ በንጋት ህንፃ እና በአዳነ ገብሩ ህንፃ በኩል ወደ ውስጥ ገባ ብሎ።
ስልክ 011-661-0069/ 011-662-1885
Tender details
- Deadline: 2026-08-10
- Bid closing time: 13:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-10 14:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: The Brooke Hospital For Animals
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 600.00 (ስድስት መቶ ብር)
- Published on: 2merkato.com (Jul 27, 2026)
- Posted at: 2026-07-27T06:35:26.000Z