Fuel, lubricants and solid fuel

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የታጠበ የሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል (Washed Local Coal) መጠኑ 10,000 (አስር ሺህ) ቶን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ ቁጥር ሙሲፋ/20/2018

የታጠበ የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል ግዢ ጨረታ

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የታጠበ የሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል (Washed Local Coal) መጠኑ 10,000 (አስር ሺህ) ቶን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በጨረታው የሚሳተፉ ድርጅቶች በዘርፉ የተሰማሩ አምራች ወይም አቅራቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ያላቸው፣ አምራች ከሆናችሁ ከክልል መንግስታት የተሰጠ የማእድን ማምረት ስራ ፍቃደ ሰርተፊኬት፤ አቅራቢ ከሆነ የአቅሪ ቢነት ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ አና የታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ ጊዜው ያላለፈበት የታክስ ክሲሪንስ ማቅረብ የሚችሉ፤ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ የድንጋይ ከሰል ምርመራ ውጤት እና ይዞታ መግለጫ ማቅረብ የሚችሉ (አስገዳጅ መስፈርት ሲሆኑ አሟልቶ ያላቀረብ ከጨረታ ይሰረዛል)፤ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች (ንግደ ምዝገባ ፤ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስና የታክስ ክፍያ ምዝገባ ኮፒ) በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 ከነቫቱ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ገርጂ አካባቢ የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል መዳረሻ ወለል ከሚገኘው የፋብሪካው ግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበረያ ዋስትና 2,000,000.00 (ሁለት ሚሊዮን ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ CPO ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋሪንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶት ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሀሴ 05 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዢ መምሪያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ ነሀሴ 05 ቀን 2018 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዢ መምሪያ ይከፈታል።

ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንት ፋብሪካ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-11
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid opening: 2026-08-11 10:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Mugher Cement Factory
  • Buyer address: Addis Ababa, Ethiopia
  • Bid bond: 2,000,000.00 ብር
  • Bid document price: 575.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jul 26, 2026)
  • Posted at: 2026-07-27T06:46:22.000Z
← Back to all tenders