Architectural and urban planning

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የአየር ማረፊያ ማስተር ፕላኒንግ እና የመሬት አጠቃቀም ጥናት የምክር አገልግሎትን ደረጃ 1 የመንገድ ወይም አጠቃላይ አማካሪ የሆኑ የሀገር ውስጥ ጨረታ ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው የሀገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ -SSNT-T627

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በሀገር ውስጥ ለሚገኙ ዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ አየር ማረፊያዎቹ በስድስት (6) ምድቦች በማደራጀት የአየር ማረፊያ ማስተር ፕላኒንግ እና የመሬት አጠቃቀም ጥናት የምክር አገልግሎትን ደረጃ 1 የመንገድ ወይም አጠቃላይ አማካሪ የሆኑ የሀገር ውስጥ ጨረታ ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው የሀገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለማስራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ብቁ የሆኑ አማካሪዎችን ስራውን ለማከናወን ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል። የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ በዘርፉ የታደሰ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች በሁለት ምድቦች ውስጥ መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን ሊያሸንፉ የሚችሉት ግን አንድ ምድብ ላይ ብቻ ይሆናል። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277( E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNI-1627 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Ship Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000.00 / ሁለት መቶ ሺህ ብር / በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ለ150 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።

የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ ሥራው ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ በ180 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ይሆናል። ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጨረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ዓርብ, ነሐሴ 15 2018 ዓ.ም እስከ 8:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ 8:30 ሰዓት ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ:- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-517-8025
ኢ-ሜይል: [email protected] 
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


Tender details

  • Deadline: 2026-08-21
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-08-21 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
  • Buyer TIN: 0000028498
  • Bid bond: 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Jul 26, 2026)
  • Posted at: 2026-07-27T08:00:07.000Z
← Back to all tenders