Roads, highways and asphalt works
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የDC-4 ያልተነጠፈ የአደጋ ጊዜ መዳረሻ መንገድ ዲዛይንና ግንባታ ፕሮጀክትን በዲዛይን ግምገማ እና ግንባታ(Design Build of Unpaved DC-4 Emergency Access Road Construction at Gondar and Gambella Airports Project) የውል ዓይነት በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር SSNT-T626
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ 2 እና ከዚያ በላይ የጠቅላላ እና የመንገድ ስራ ተቋራጭ (GC/ RC2 and above) የሆኑ የሀገር ውስጥ ጨረታ ለመሳትፍ ፈቃድ ያላቸው የሀገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ በጎንደር እና ጋምቤላ አውሮፕላን ማረፊያዎች የDC-4 ያልተነጠፈ የአደጋ ጊዜ መዳረሻ መንገድ ዲዛይንና ግንባታ ፕሮጀክትን በዲዛይን ግምገማ እና ግንባታ(Design Build of Unpaved DC-4 Emergency Access Road Construction at Gondar and Gambella Airports Project) የውል ዓይነት በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ፣ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የታደሰ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከተፈቀደለት አካል በተጠቀሰው ምድብ ማቅረብ የሚችሉ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ (PPPAA) የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277( E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNI-626 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 / አምስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ለ150 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጨረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ዓርብ, ነሐሴ 15 2018 ዓ.ም እስከ ከረፋዱ 05:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መከፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከረፋዱ በ 05:30 ሰዓት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ:- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-517-8025
ኢ-ሜይል: [email protected]
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Tender details
- Deadline: 2026-08-21
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-08-21 11:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
- Buyer TIN: 0000028498
- Bid bond: 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Jul 26, 2026)
- Posted at: 2026-07-27T08:04:37.000Z