Cleaning and janitorial services
በአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር -ፈ/ህ/አጠ/ስፔ/ሆ-001/19
በአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
- ምድብ 1. የህትመት ስራ ፣
- ምድብ 2. የኦአር ልብስና ራቨር ሽት ፣
- ምድብ 3. የኤሌትሮኒክስ እቃዎች ፣
- ምድብ 4. የጥበቃ አዉትሪሶርስ ስራ፣
- ምድብ 5. የግቢ የፅዳት አገልግሎት እና
- ምድብ 6. የአልባሳት እጥበት ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ፣ ለመግዛት እና ተ.ቁ 4 ፣5 እና 6 ለሁለት አመት እና ከዚያ በላይ ውል ይዞ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም የሚከተሉት መስፈርቶችን አሟልታችሁ በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1.በዘመኑ የታደሰና በዘርፋ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2.የግብር ከፋይነት መለያ /TIN CARD/ሰርተፍኬት ያላቸው እና ተ.ቁ 4፣5 እና 6 ከመንግስታዊ መ/ቤት/ድርጅት/ የሰሩበት በዘርፉ የሁለት አመት የስራ ልምድ መቅረብ ሚችሉ፣
3.አጠቃላይ የገንዘቡ መጠን ከብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር /እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
4.ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተቁ 1- 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5.አጠቃላይ ስለ ጨረታው ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል።
6.ተጫራቾች በጨረታው ምድብ 1. የህትመት ስራ ፣ምድብ 2. የኦአር ልብስና ራቨር ሽት ፣ምድብ 3. የኤሌትሮኒክስ እቃዎች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በመሙላት መወዳደር ይችላሉ።፣ምድብ 4. የጥበቃ አዉትሪሶርስ ስራ፣ምድብ 5. የግቢ የፅዳት አገልግሎት እና ምድብ 6. የአልባሳት እጥበት ስራ እቃዎች ሙሉ በሙሉ በመሙላት መወዳደር ይችላሉ።
7.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በ500.00/አምስት መቶ ብር/ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሆስፒታሉ ማግኘት ይችላሉ።
8.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማንኛውንም ግብር ጨምሮ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2%/ሁለት ፐርሰንት/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ዋናውን ደረሰኝ ከፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
9.ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአማርኛ ቋንቋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያው ቅፅ መሰረት የአንዱን ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ድምር ዋጋ በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሆስፒታሉ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 ቀናት 4:15 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።ሳጥኑም በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡15 ይታሸጋል።
10.ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል። ቀኑ በዓል /ዝግ /ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
11.ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12.በጨረታው የሚሳተፉ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ /ማብራሪያ/ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 3205738/058 222 0916 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ፡ፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
ባህር- ዳር
የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-08-10
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 ቀናት 4:15 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-10 12:00
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 ቀናት 4:30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Felegehiwot General Specialized Hospital
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Jul 26, 2026)
- Posted at: 2026-07-27T08:12:12.000Z