Addis Ababa

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ቱሉ ኤጀርሳ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት አመት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የግዥ መለያ ቁጥር 001-2019 ዓ.ም.

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ቱሉ ኤጀርሳ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት አመት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ የሲፒኦ መጠን 25,000
  • ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች የሲፒኦ መጠን 50,000
  • ሎት 3 የጽዳት እቃ -የሲፒኦ መጠን 30,000
  • ሎት 4 ቋሚ የቢሮ እቃዎች -የሲፒኦ መጠን 50,000
  • ሎት 5 የመኪና ጎማና ጌጣጌጦች- የሲፒኦ መጠን 10,000
  • ሎት 6 ሞንታሮቦና ዲኮሬሽን ኪራይ የሲፒኦ መጠን 3,000.00
  • ሎት 7 ህትመት ስራዎች- የሲፒኦ መጠን 5,000
  • ሎት 8 መስተንግዶ -- የሲፒኦ መጠን 5,000
  • ሎት 9 የቢሮ እቃዎች ጥገና
  • ሎት 10 የጉልበት ስራዎች
  • ሎት 11 የህዝብና የጭነት ትራንስፖርት

ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላችሁ ተጫራቾች (አቅራቢዎች)

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
  2. የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  3. ከንግድ ጽ/ቤት የተሰጣቸው የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  4. ተጫራቾች ከላይ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በእያንዳዱ ሎት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከሎት 1 እስከ ሎት8 በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ ብር ) በመክፈል ፋይናንስ ጽ/ቤት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ (ኤንቨሎፕ) ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በፋይናንስ ጽ/ቤት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን 11፡30 ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰአት ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸውና ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች እንዲሁም ለቋሚ እቃዎች ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው የፍላጎት መግለጫ መሰረት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  9. አቅራቢዎች ለተወዳደሩበት እቃዎች ማሸነፍዎን ሲያረጋግጡ ውል ማስከበሪያ 10 ፐርሰንት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  10. አምራች የሆናችሁ አቅራቢዎች ካደራጃችሁ አካል /ተቋም/ በሚመለከተው አካል የተፈረመ የዋስትና ደብዳቤ እና አምራች ስለመሆናችሁ ማረጋገጫ ደብዳቤ ማምጣት ትችላላችሁ። አምራች ያልሆናችሁ አቅራቢዎች በዋስትና ደብዳቤ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን።
  11. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
  12. የዘገየ ተጫራችና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም
  13. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  15. አድራሻ - ን/ስ/ላ/ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከጋርመንት ወደ አትክልት አሜን ሆቴል ወደ ውስጥ ገባ ብሎ አባ ገዳ ሳይደርስ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍስ ከተማ ወረዳ 14 የቱሉ ኤጀርሳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-06
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን 11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-07 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰአት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: NIfas Silk Lafto Sub City Woreda 14 Tulu jeresa Woreda FEDB
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Jul 27, 2026)
  • Posted at: 2026-07-27T09:17:39.000Z
← Back to all tenders