Guarding and manned security services

አራዳ አትክልት ተራ የገበያ ማእከል አ.ማ. የጥበቃ አገልግሎት በዘርፉ ለተሰማሩ የጥበቃ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ መስጠትና ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
የጥበቃ ሰራተኞች ቅጥር ለማከናወን ተጫራች ድርጅቶችን
ለማወዳደር የመወዳደሪያ መስፈርት

ድርጅታቻን አራዳ አትክልት ተራ የገበያ ማእከል አ.ማ. በተለምዶ ፒያሳ አትክልት ተራ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ 2B+SB+G+9 ህንፃ ገንብቶ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል፤ በመሆኑም የህንፃውን የጥበቃ አገልግሎት በዘርፉ ለተሰማሩ የጥበቃ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ መስጠትና ማሰራት ይፈልጋል

በዚህ መሰረት ተጫራቾቹ የሚከተሉትን መስፈርት ማሟላት ይጠበቅበታል፡-

1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ

2. የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ

3. የታደስ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፤

4. በዘርፉ ከ10/አስር/ አመት በላይ የሥራ ልምድ ያለው፤

5. በሥራ ወቅት ለሚደርሱ አደጋዎችና ችግሮች የኢንሹራንስ ሽፋን የተገባ መሆኑን

6. በዘርፉ የሰለጠኑና ብቃት ያላቸውን የሰው ኃይል ማቅረብ የሚችሉና በፈረቃ (በወጪ ገቢ) የሚሰሩ

7. በተገቢ ሁኔታ የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) ለሰራተኞቹ የሚያቀርብ እና

8. እስካሁን ከሰራባቸው ድርጅቶች የመልካም የሥራ አፈፃፀም ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት::

ተጫራቶች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አክሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 024 በመቅረብ ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ በመክፈል መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን:: ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺ ብር/ በሲ.ፒ.ኦ ከጨረታው ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤

ጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሀሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት በ8፡00 ሰዓት ይከፈታል፤

አከሲዮን ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0935 401595/96ማግኘት ይቻላል

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ ክ/ከተማ አራዳ ወረዳ 1 የቤ.ቁ አዲስ ፒያሳ አትክልት ተራ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-10
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ
  • Bid opening: 2026-08-27 14:00
  • Bid opening (note): ነሀሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት በ8፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Arada Atkilt Tera Market Center S.C.
  • Bid bond: 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) ብር
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Reporter (Jul 26, 2026)
  • Posted at: 2026-07-27T09:26:50.000Z
← Back to all tenders