Labour outsourcing and staffing
ፀሐይ ባንክ አ.ማ. ለባንኩ ሁሉም ቅርንጫፎች የጽዳት ሰራተኛ አቅርቦት /ከነመስሪያ ግብዓቶቹ/፣ መኪና አጣቢ እና የጉልበት ሰራተኛ ይፈልጋል
Labour outsourcing and staffingLabour Outsourcing ServicesCleaning and Janitorial Equipment and Service
Addis Ababa
More tags
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ፀባ/003/2018
ፀሐይ ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች ለተገለጹት የስራ ዓይነቶች የሰው ኃይል በማቅረብ አግባብ ካለው ፈቃድ ሰጪ የመንግስት ተቋም ሙያዊ ፍቃድ ያላቸውን ድርጅቶችን በማወዳደር የሠራተኛ አቅርቦት ግዢ ማከናወን ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የስራው/የአገልግሎቱ ዓይነት |
|
1 |
ለባንኩ ሁሉም ቅርንጫፎች የጽዳት ሰራተኛ አቅርቦት /ከነመስሪያ ግብዓቶቹ/ |
|
2 |
መኪና አጣቢ |
|
3 |
የጉልበት ሰራተኛ |
በጨረታው የሚወዳደሩ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል
- ከሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የቅጥር/employment/ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዶቹ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ ቅጅ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የቲን የምስክር ወረቀት እና ከገቢዎች ሚኒስቴር ከግብር ነፃ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ቀናት ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሶስት ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት የማይመለስ ሶስት መቶ ብር /300.00/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ ነሐሴ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ በዋና መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 9፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ /Bid Bond/ የሚሆን ብር 50,000.00 በባንክ በተመሰከረለት የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ዋስትናውም ቢያንስ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሊሆን ይገባዋል።
- የጨረታው መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች በስራው/ዘርፉ ለ2 ዓመታትና ከዚያ በላይ የቆየ መሆን አለበት፤ ከሁለት ዓመት በታች ልምድ ያለው ድርጅት ተቀባይነት አይኖረውም።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ
- በስልክ ቁጥር +251 11 470 6033 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ። በአካል በመቅረብ መረጃ ማግኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት፣ መዓዛ ደሳለኝ ህንፃ 5ኛ ፎቅ የባንኩ ፋሲሊቲስ ማኔጅመንት መምሪያ ማግኘት ይችላሉ።
Tender details
- Deadline: 2026-08-14
- Bid closing time: 15:00
- Bid opening: 2026-08-14 15:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Tsehay Bank S.C.
- Buyer address: Beklobet, Meaza Desalegn Building (In front of Ethiopia Hotel #2), 5th floor
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Reporter (Jul 26, 2026)
- Posted at: 2026-07-27T11:00:46.000Z