Military, police and guard uniforms
ትረስት የጥበቃና የሰው ኃይል አገልግሎት ኃ.የተ.የግ.ማህበር የደንብ ልብስ በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል
Description
ትረስት የጥበቃና የሰው ኃይል አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
የደንብ ልብስ ጨረታ ማስታወቂያ
ትረስት የጥበቃና የሰው ኃይል አገልግሎት ኃ.የተ.የግ.ማህበር በተለያየ ሙያ ላሰማራቸው ሠራተኞች በቂ ሙያና ልምድ ባላቸው ድርጅቶች መ/ቤታችን በሚያቀርበው የስፌትና የጨርቅ ናሙና መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የደንብ ልብሶች ማቅርብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- መደብ 1 ዩኒፎርም 7,000
- መደብ 2 ጃኬት 1,000
- መደብ 3 ቲሸርት 3,000 በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል። ይህም የአገልግሎት ግዥ የስፌት አገልግሎቱን እስከነ ጨርቁ ዋጋ ያጠቃለለ ይሆናል።
ስለሆነም፡-
1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሠርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከብስራተ ገብርኤል ወረድ ብሎ ሎሊ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት መግዛት ይችላሉ፣
3. ተጫራቾች ይህ ማሰታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ከሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ነሀሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 20 የስራ ቀናት ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ውሰጥ በሚቀረበው ናሙና መሠረት የዋጋ ዝርዝር በመሙላትና የጠቅላላ ዋጋውን 5% የጨረታ ማስረከበያ ሲፒኦ በማካተት በዋናው ቢሮ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ሃያ/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ጧት ከ2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ20ኛው (ነሀሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም) የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና ከቀኑ 8፡05 ይዘጋና በዚያው እለት ከሰዓት በኋላ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኩሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ዋና ቢሮ ይከፈታል።
6.ተጫራቾች ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ስራ ከሰሩበት ድርጀት ስለሰጡት አገልግሎት የሚጠቅስ መልካም የስራ አፈፃፀም ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7 ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻችን፡-
ከብስራተ ገብርኤል ወረድ ብሉ ሎሊ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ስልክ ቁጥር 0113729118/0911162478 ይጠቀሙ
Tender details
- Deadline: 2026-08-21
- Bid closing time: 14:05
- Bid opening: 2026-08-21 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Trust Security and Human Resource Service P.L.C.
- Bid bond: 5%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Reporter (Jul 26, 2026)
- Posted at: 2026-07-27T12:20:51.000Z