Fuel, lubricants and solid fuel
የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውል የማገዶ እንጨት በዘርፉ ከተሠማሩ ነጋዴዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውል የማገዶ እንጨት በዘርፉ ከተሠማሩ ነጋዴዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ይችላሉ፡-
1. በዚህ ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና ለአቅራቢነት የተመዘገቡ የንግድ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
2. በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የሚገለጸውን ማገዶ እንጨት ለ6 ወራት የሚፈለገው መጠን ጥራትንና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በየወሩ እስከ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ድረስ አምጥተው ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
3. ማንኛውም ተጫራች በተራ ቁጥር 1 የተገለፁትን ህጋዊ ማስረጃዎች ለጨረታው ከሚቀርበው ዋጋ ጋር ዋናውንና ኮፒውን አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበርያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ በባንክ በተረጋገጠ CPO 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር ከዋናው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. የጨረታው ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎኘ በሰነድ ላይ በተገለፀው አድራሻ በተከታታይ 15 ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው በአስራ አምስተኛ ቀን በ4፡00 ሰዓት ሲሆን የጨረታ ሳጥን የሚከፈተው በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ይከፈታል ይህ ቀን የበዓልም ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
7. ማንኛውም ተጫራች ማገዶ እንጨት ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ አንድ ቀን ቀደም አድርጎ በማስገባት ጥራቱን ለጨረታ ኮሚቴ ማሳየት አለበት፡-
8. ተጫራቾች ከሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/ሥ/ሂደት ቀርበው ዝርዝር ሰነዱን 200 (ሁለት መቶ) ብር በማይመለስ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል።
ማሳሰብቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር፡- 046-212-87-47 መደወል ይችላሉ።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግስት ሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም
Tender details
- Deadline: 2026-08-11
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው በአስራ አምስተኛ ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-11 14:30
- Bid opening (note): የጨረታ ሳጥን የሚከፈተው በአስራ አምስተኛ ቀን በ8፡30 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Hawassa Central Prison Institute
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Jul 28, 2026)
- Posted at: 2026-07-28T08:29:07.000Z