Imaging and diagnostic equipment

የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዘድ ሆስፒታል Uitrasound-General purpose, color Dopplermobile, 4D machine በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዘድ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል

1, Ultrasound-General purpose, color Dopplermobile,4D machine በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

  • በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር እንዲሁም የኢትዮጵያ የምግብና የመድሃኒት ጤና እንክብካቤ አስተዳደር የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከሆስፒታሉ ገንዘብ ቤት መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች  የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦሪጅናሉንና ኮፒ በጥንቃቄ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፣
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትንuitrasound-Generalpurpose,colorDopplermobile,4D machine አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፣
  • ተጫራቾችየሚወዳደሩባቸዉንuitrasound-Generalpurpose,colorDoppler,mobile,4D machine በሆስፒታሉ የጨረታ ሰነድ አይነትና ዝርዝር /ስፔስፊኬሽን/ መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች ያሸነፉበትን Ultrasound-General purpose, color Dopplermobile,4D machine ሙሉ በሙሉ በራሳቸው ትራንስፖርት ሆስፒታሉ ድረስ በተፈለገ ጊዜ የማቅረቢያ ደብዳቤ ሲደርሳቸው ወዲያውኑ በማቅረብ ማስረከብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች ሆስፒታሉ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ይህ ማለት በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ ማቅረብ አይችሉም።
  • ተጫራቾች ሆስፒታሉ
  • ተጫራቾች ያሸነፉበትን ሲያቀርቡ ባሸነፉበት ጥራትና ዋጋ ዝርዝር መሰረት ልዩነት ቢኖረውና የጥራት ችግር ቢከሰት በራሳቸው ወጭ እንደገና የመተካት ግዴታ አለባቸው።
  • ተጫራቾች ያሸነፉትን ትክክለኛነቱን ሆስፒታሉ በሚመለከታቸው ባለሞያዎችና ሃላፊዎች በማረጋገጥ ይረከባል።
  • ተጫራቾች ያሸነፉትን Ultrasound-General purpose, color Doppler,mobile,4D machine የሁለት ዓመት ዋስትና መስጠት እንዱሁም ለባለሙያዎችና ለሚመለከታው ስልጠና መስጠት አለባቸው።
  • ተጫራቾች ያሸነፉትን Ultrasound-General purpose, color Dopplermobile,4D machine service training, user training, installation and Commisiong phat አለባቸው።
  • ተጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 100,000/አንድ መቶ ሺህ ብር/ እና ካሸነፉ በኋላ ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ዋስትና ማስከበሪያ መሰረት ማስያዝ አለባቸው በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ፣ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ በባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆስፒታሉ ገንዘብ ቤት ድረስ ቀርበው ማስያዝ አለባቸው።
  • ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ውስጥ የውል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10%በማሲያዝ በውልና ማስረጃ ውለታ በመፈፀም ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች ከአሸነፋ በኋላ ሚያሲዙት የጨረታ ውል ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ከሆነ የግዜ ቆይታው 12ወር መሆን አለበት፡፡
  • ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት አየር ላይ ቆይቶ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ማስገባት ይችላሉ፡፡የጨረታ ሳጥኑ 4፡00 ይታሸጋል በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን በዓላት ቀን ከሆነ በቀጣይ ስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል።
  • የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ60 ቀን ፀንቶ ይቆያል።
  • ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት፣ በስልክ ቁጥር 0116813390 ወይም 0116376994 በፋክስ 0116811008 ቁጥር በመላክ መጠየቅ ይቻላል።
  • መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን በሙሉ የመሠረዝ መብቱ እንዲሁም ግዥውን በጥቅል ወይም በተናጠል አወዳድሮ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።

ደብረ ብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-08-12
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት አየር ላይ ቆይቶ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-12 10:30
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት አየር ላይ ቆይቶ 16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Debrebirhan Specialized Hospital
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jul 28, 2026)
  • Posted at: 2026-07-28T12:11:51.000Z
← Back to all tenders