Catering and cafeteria services

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ለዋና ጠቅላይ መምሪያው ጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚውል ቀለብ በሎት ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አመታዊ ውል ይዞ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2018

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በ2019 በጀት አመት ለዋና ጠቅላይ መምሪያው ጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚውል ቀለብ በሎት ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አመታዊ ውል ይዞ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና የሚወዳደሩበት ሎት ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ የተጫራቾች መመሪያውንና የቀለብ ዝርዝር የሚገልጽ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ዝርዝር ሰነድ በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር /በመክፈል በአማራ ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 13 መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ 50,000.00 /ሀምሳ ሺህ ብር/ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ከፈለጉ ማስረጃውን /የገቢ ደረሰኙን / ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከፋይናንስ /ዋጋ ማቅረቢያ/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  4.  ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ በተጫራቾች መመሪያ ላይ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው ላይ በእያንዳንዱ ገጽ ማህተማቸውን እና ፊርማቸውን በማስፈርና ፖስታውን በሚገባ በማሸግ የአማራ ፖሊስ ዋናዉ መስሪያ ቤት ግዥ ባለሙያዎች ቢሮ ቁጥር 06 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 የሚዘጋ ሲሆን በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 የሚከፈት ይሆናል፡፡
  7.  የርክክብ ቦታ ባሕር ዳር ከተማ መ/ቤቱ ድረስ በግንባር በመቅረብ ይሆናል፡፡
  8.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0918028175/0977135678 ባሕር ዳር ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት
ባህር ዳር


Tender details

  • Deadline: 2026-08-11
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-11 14:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara Region Police Commission
  • Buyer address: ባህር ዳር ቀበሌ 16 ከቴሌና ሲቪል ሰርቪስ ማዕከል አብክመ ልዩ ሃይል ፖሊስ ም/ዘርፍ ግዥ ቢሮ ቁጥር 11
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Be'kur (Jul 27, 2026)
  • Posted at: 2026-07-29T05:59:32.000Z
← Back to all tenders