Catering and cafeteria services

የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል የምግብ አቅርቦት እንዲሁም የልብስ እጥበት አገልግሎት ማቅረብ/ ማስቀረብና ማሳጠብ ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ


በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2019 የበጀት አመት አመቱን ሙሉ ተኝተው ለሚታከሙ ታካሚዎች

  • ሎት 1. የምግብ አቅርቦት እንዲሁም
  •  ሎት 2. የልብስ እጥበት አገልግሎት ማቅረብ ማስቀረብና ማሳጠብ ይፈልጋል፡፡

 ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የቫት ተመዚጋቢ የሆኑ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እና የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የሚቀርቡ የምግብ እና የሚታጠቡ የልብስ እጥበት አይነት አገልግሎት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ስዓት በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ እና ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ወይም መግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የእቃው ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ ባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ወይም ሲፒኦ ማሰያዝ አለባቸው ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታውን በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ማለትም ከሐምሌ 20/2018 እስከ ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም ጀምሮ መውሰድ እና መመለስ የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ማለትም ነሐሴ 06/2018 ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ እና ፋይናንስ ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. አሸናፊው የሚለየው በሎት ዋጋ ነው ፡፡
  9. አሸናፊው አገልግሎቱን ማቅረብ ያለበት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰጠውን የምግብ እና የልብስ እጥበት ዝርዝር እንጅ ሥርዝ /ድልዝ/ ወይም ሌላ ተመሳሳይ እቃ ማቅረብ አይችልም፡፡
  10. አሸናፊ ድርጅቱ በምዕራብ ጎንዳር ዞን ፍትህ መምሪያ ቀርቦ ውል መውሰድ አለበት፡፡
  11. መ/ቤቱ ከተጠየቀው 20 በመቶ ከፍ ወይም ዝቅ ማለት ይችላል፡፡
  12. በመ/ቤቱ ለምግብ እና ለእጥበት ለአሸናፊው የሚሰጠው መብራት፣ ውሀ እና ቤት ኪራይን በነፃ ሲሆን ከግቢ ውስጥ የመብራት እና የውሀ መጥፋት ቢገጥም በራሳቸው የሚያቀርቡ መሆኑን እየገለፅን ይሄን ታሳቢ በማድረግ ዋጋውን እንድትሞሉ ያሳውቃል፡፡
  13. አሸናፊው ድርጅት በመ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ባለው የምግብ ቤት እና የላውንደሪ ቤት ገብቶ መስራት ይጠበቅበታል፡፡
  14. አሸናፊው በመስሪያ ቤቱ ባለው የስነምግብ ባለሙያ በሚያቀርበው የሰው ሀይል ብዛት ብቻ ምግብ ማቅረብ አለበት፡፡
  15. የልብስ እጥበት በሚከፈለው ቆሽሽው በታጠቡ ልብሶች ብዛት ይሆናል፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  17. ስለጨረታው ዝርዘር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 331 00 54 /058 331 01 75 መደወል ይችላሉ፡፡

የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-08-12
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-12 10:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Metema General Hospital
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Be'kur (Jul 27, 2026)
  • Posted at: 2026-07-29T06:10:30.000Z
← Back to all tenders