Disposal, scrap and surplus sales
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ እቃዎች በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ሐራጅ ጨረታ ቁጥር 03/2018/19 ዓ.ም.
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው ሸቀጣሸቀጥ(ልዩ ልዩ)፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ poly(ethylene terephtalate) plastic cas(ጥሬ ፕላስቲክ)፣ ኮስሞቲክስ፣ የኮንስትራክሽን ማቴሪያል እና የኮንስትራክሽን ማቴሪያል(የቦንባ እቃዎችን) በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ኘሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን ፡-
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-
1. ለጨረታ በቀረቡት እቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው እቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል። ማንኛውም ተጫራቾች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።
2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ እቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።
3. የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የእቃዎቹን ዝርዝር፣ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሰነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል።
4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚወጣበት ቀን እና የሚያበቃበት እንዲሁም ሰዓት የሚያሳይ ሰንጠረዥ፡-
|
ተ.ቁ |
የእቃው አይነት |
የጨረታው አይነት |
በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመበት ቀን |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
ጨረታው የሚጀመርበት ሰዓት |
ጨረታው የሚከፈትበት ሰዓት |
ስልክ ቁጥር
|
|
1 |
ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) |
ሐራጅ |
22/11/2018 |
27/11/2018 |
4:00 |
8:00 |
0221118429/0222118925 |
|
2 |
ኤሌክትሮኒክስ |
ሐራጅ |
22/11/2018 |
27/11/2018 |
4:00 |
8:00 |
0221118429/0222118925 |
|
3 |
POLY (ETHYLENE TEREPHTHALATE) PLASTIC CAS (ጥሬ & ፕላስቲክ) |
ሐራጅ
|
22/11/2018 |
27/11/2018 |
4:00 |
8:00 |
0221118429/0222118925
|
|
4 |
ኮስሞቲክስ |
ሐራጅ |
22/11/2018 |
27/11/2018 |
4:00 |
8:00 |
0221118429/0222118925 |
|
5 |
የኮንስትራክሽን ማቴሪያል |
ሐራጅ |
22/11/2018 |
27/11/2018 |
4:00 |
8:00 |
0221118429/0222118925 |
|
6 |
የኮንስትራክሽን ማቴሪያል (የቧንቧ እቃዎች) |
ሐራጅ
|
22/11/2018 |
27/11/2018 |
4:00 |
8:00 |
0221118429/0222118925 |
4. በጨረታው ሽያጭ የእቃዎቹ አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆኑ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም፡፡
5 .በሐራጅ ጨረታ ለምትወዳደሩ ለጨረታው ዋስትና የሚሆን ማለትም፤
- ለምድብ 01, ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) ብር 77,800.00፣
- ለምድብ 02, ኤሌክትሮኒክስ ብር 211,200.00 ፣
- ለምድብ 03, ኤሌክትሮኒክስ ብር 67,500.00 ፣
- ለምድብ 04, poly(ethyleneterephtalate) plastic cas(ጥሬ ፕላስቲክ) ብር 67,600,00 ፣
- ለምድብ 05, ሸቀጣሸቀጥ(ልዩ ልዩ) ብር 33,300.00 ፣
- ለምድብ 06, ሸቀጣሸቀጥ(ልዩ ልዩ) ብር 191,500.00፣
- ለምድብ 07, ኮስሞቲክስ ብር 110,200.00 ፣
- ለምድብ 8, ኮስሞቲክስ ብር 114,000.00፣
- ለምድብ 9 ኮስሞቲክስ ብር 406,400.00 ፣
- ለምድብ 10, ኮስሞቲክስ ብር 116,000.00፣
- ለምድብ 11, የኮንስትራክሽን ማቴሪያል ብር 213,500.00 ፣
- ለምድብ 12, ኮስሞቲክስ ብር 849,300.00፣
- ለምድብ 13, ኮስሞቲክስ ብር 18,300.00 ፣
- ለምድብ 14, ሸቀጣሸቀጥ(ልዩ ልዩ) ብር 203,400.00፣
- ለምድብ 15, ኮስሞቲክስ ብር 204,500.00 ፣
- ለምድብ 16, ኤሌክትሮኒክስ ብር 1,439,100.00፣
- ለምድብ 17, የኮንስትራክሽን ማቴሪያል(የቧንቧ እቃዎች) ብር 219,400.00 ፣
- ለምድብ 18, ኤሌክትሮኒክስ ብር 119,100.00 ፣
- ለምድብ 19, ኤሌክትሮኒክስ ብር 73,000.00 ፣
- ለምድብ 20, ኮስሞቲክስ ብር 23,600.00 እና
- ለምድብ 21, ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) ብር 127,100.00 በ(Customs Commission Adama Branch) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ.በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
6. በሐራጅ ጨረታ ለመሸጥ የወጡትን እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የውርስ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 6 (ስድስተኛው) ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማየት እና መጫረት ይቻላል።
7. በሐራጅ ጨረታ የእቃዎቹ የመነሻ ዋጋ ያልተወሰነላቸው ስለሆነ የመነሻ ዋጋ በተጫራች የሚሰጥ ይሆናል።
8. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን፤ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 /ሶስት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
10. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም።
11. ከላይ በተ/ቁ 9 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
12. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን።
NB: በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን መረጃዎች ያላሟላ ተጫራች ቢያሸንፍ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ ለመንግስት ገቢ የሚደረግ እና እቃው በድጋሚ ጨረታ ላይ የሚወጣ መሆኑን እናሳውቃለን።
የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-5511/ 011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- አዳማ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የውርስ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች
0221118429 እና 0222118925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-03
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-08-03 14:00
- Region: Oromia
- Publishing entity: Adama Custom Commission Branch Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Jul 29, 2026)
- Posted at: 2026-07-29T08:45:18.000Z