Addis Ababa
አንድ ሚሊዮን ብርቱ (One Million Birtu (OMB) ኮንፕሬሄንሲቭ ሄልዝ ፖስት (Comprehensive Health Post) አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል
Description
የቤሌላ ኮንፕሬሄንሲቭ ሄልዝ ፖስት
ግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
1. የሥራው ዓላማ
አንድ ሚሊዮን ብርቱ (One Million Birtu (OMB) ሀገር በቀል ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ዋና ዓላማውም እስከ 2030 ዓ.ም የአንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ሕይወት ማሻሻል ነው። ድርጅቱ ከዘላቂ የልማት ግብ 7 (SDG 7) ጋር በተጣጣመ መልኩ ንፁሕ የኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ሁሉን አቀፍ እና ሰፊ ተደራሽነት ያላቸውን መፍትሔዎች በማቅረብ ላይ ያተኩራል።
ይህንንም ለማሳካት በጠምባሮ ልዩ ዞን፣ ሙዱላ ወረዳ ለሚገነባ ኮንፕሬሄንሲቭ ሄልዝ ፖስት (Comprehensive Health Post) ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ሥራዎች መስፈርቱን ለሚያሟሉ ብቃት ያላቸው የኮንስትራክሽን (ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች) አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
2. ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
1. ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ እና ምዝገባ፦
- የንግድ ፈቃድ፦ ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ (Renewed Trade License for 2018 EC.)
- የብቃት ማረጋገጫ፦ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል የተሰጠ የታደሰ የሥራ ተቋራጭነት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ከደረጃ GC-5 እስከ GC-6 እና ከዚያ በላይ ያላቸው (Renewed Competency Certificate of Registration -BC/GC Grade 5 to Grade 6
- የግብር ክሊራንስ፦ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል እና በጨረታው መዝጊያ ቀን የጸና የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ (Valid Tax Clearance Certificate):
- የቫት ምዝገባ፦ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ምስክር ወረቀት።
- የግብር ከፋይ ቁጥር፦ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)።
2. የሥራ ልምድ፦
- በኮንስትራክሽን እና ግንባታ ዘርፍ ቢያንስ 5 ዓመት እና ከዚያ በላይ ተዛማጅ የሥራ ልምድ ያላቸው።
3. ተመራጭ ሁኔታዎች (ተጨማሪ ነጥብ የሚያስገኙ)፦
- በጤና ተቋማት (Health Centers/Health Posts) ግንባታ ላይ ቀደም ሲል የሠሩ እና የሥራ አፈጻጸም ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
- በኮምፕረስድ አርዝ ብሎክ (Compressed Earth Block - CEB) ቴክኖሎጂ ግንባታ ላይ ልምድ ወይም እውቀት ያላቸው።
- በገጠር እና አስጋሪ አካባቢዎች ፕሮጀክቶችን በውል ጊዜ ውስጥ የማጠናቀቅ ልምድ ያላቸው።
3. የማመልከቻ ዝርዝሮች
- የጨረታ ሰነድ ማግኛ፦ ፍላጎት ያላቸው ተወዳዳሪዎች ሙሉ የሥራ መግለጫ (Statement of Work) እና አጋዥ ሰነዶችን [email protected] ስልክ፡ +251 9443687 በመጠየቅ ወይም በግንባር በመገኘት ማግኘት ይችላሉ።
- የጨረታ ማቅረቢያ ቦታ፦ የታሸጉ እና ማኅተም የተደረገባቸው የቴክኒክ እና የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያዎችን በግንባር በሚከተለው አድራሻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፦
አድራሻ፦ ቦሌ መድኃኒዓለም፣ አቢሲኒያ ፕላዛ፣ 10ኛ ፎቅ፣ አዲስ አበባ።
- የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት፦ ጨረታው ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም (August 14, 2026) ከቀኑ 11:00 ሰዓት ይዘጋል። (ከዚህ ሰዓት ዘግይተው የሚመጡ ማመልከቻዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም)።
አንድ ሚሊዮን ብርቱ
Tender details
- Deadline: 2026-08-14
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-08-14 17:00
- Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: One Million Birtu (OMB)
- Published on: Addis Zemen (Jul 29, 2026)
- Posted at: 2026-07-29T09:27:54.000Z