Electrical installation and wiring

በጅማ ዞን የሸቤ ሶንቦ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ አቅርቦት እና የኢንስታሌሽን ስራና የስልጠና ማዕከል አገልግሎት (MESOB) በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በጅማ ዞን የሸቤ ሶንቦ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት

  • የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ አቅርቦት ፣
  • የኢንስታሌሽን ስራና የስልጠና ማዕከል አገልግሎት (MESOB)

በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል።

ስለዚህ በዚህ ጨረታ ላይ ስመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ፍቃድ የሳደሱ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ እና TIN No. ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሰርተፍኬት ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  3. ተጫራቾች በሥራው ንግድ ዘርፍ ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል የጨረታን ጠቅላላ ዋጋ 10% ከተረጋገጠ ባንክ በ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነደ ከሸቤ ሶንቦ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 500 በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዳስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ቅዳና እና እሁድን ጨምሮ በተከታታየ ለ10 ቀናት መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራች VAT እና TOT ን ለመከፈል ፍቃደኛ የሚሆን መሆን አለበት።
  7. ተጫራቾች አስፈላጊውን ሰነድ ማለትም ቴክኒኩንም ፋይናሸሉንም በተለያየ ፖስታ ውስጥ ከቶ ፎቶ ኮፒውን በአንድ ፖስታ ውስጥ ከተው ኦሪጅናሉን ደግሞ በሌላ አንድ ፖስታ ውስጥ ከተው ፖስታዎቹን በሰም አሽገው ላዩ ላይ ፈርመው ማህተም አድርገውበት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 10ኛው ቀን 11፡30 /አስራ አንድ ሰዓት ተኩል ጨርሰው የሚዘጋ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ልክ ከጠዋቱ በ3፡00ሰዓት ይሆናል።
  8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ አስተያየት በስልክ ቁጥር 0922711225 ደውሎ ማረጋገጥ ይቻላል።

በጅማ ዞን የሸቤ ሶንቦ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-08
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-10 09:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ልክ ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Jimma Zone Shebe Sonbo Woreda FEDB
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jul 30, 2026)
  • Posted at: 2026-07-30T09:56:31.000Z
← Back to all tenders