Catering and Cafeteria Services
ቤኬ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2019 በጀት አመት የመምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ካፌ ሁለቱንም ተቋም (ቤኬ ቅድመ አንደኛ እና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በአንድ ላይ) የካፍቴርያ አገልግሎት በማጫረት ማሰራት ይፈልጋል
Description
የካፌ ጨረታ ማስታወቂያ
ቤኬ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2019 በጀት አመት የመምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ካፌ ሁለቱንም ተቋም (ቤኬ ቅድመ አንደኛ እና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በአንድ ላይ) የካፍቴርያ አገልግሎት በማጫረት ማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ በዚህ ጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በሙሉ ማሟላት ያለባቸሁ
መስፈርቶች፡-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
- በዘመኑ ግብር ስለመክፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይነት መለያ TIN ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
- ለሚሰጠው አገልግሎት ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል
- በመስሪያ ቤቱ ህግና ደንብ መሰረት ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ
- ከዚህ በፊት ቁርስና ምግብ ቤት ስራ ላይ መሳተፋቸውን የሚገልፅ መረጃ የሚያቀርቡ
- CPO/Bid Bond የ5000 ሺህ ብር በባንክ የተረጋገጠ በቤኬ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስም የተዘጋጀ ማስያዝ የሚችል።
ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን ከቤኬ ቅ/አ፣ አንደኛና መ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል በ100 ብር እየገዛችሁ ከዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ጋር አባሪ ያደረግነውን የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ በመውሰድ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 28 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ሞልታችሁ እንድታስገቡ በማለት እንገልፃለን፡፡ ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዛው ቀን 4፡30 ይከፈታል።
ማሳሰቢያ
- ት/ቤቱ ውሃና መብራት የሚሸፍን መሆኑን እናሳውቃለን
- እንዲሁም በካፌው ውስጥ ያሉ የመገልገያ እቃዎች እንደ፡-ፍሪጅ
- ወንበር ከነጠረንቤዛው ሙሉ
- 43ኢንች ቲቪ
- የውሃ ሮቶ
- ባነኮኒ እና መደርደሪያ ሸልፍ የመሳሰሉት እቃዎች ያሟላና የቤት ኪራይ በነፃ መሆኑን አውቃችሁ ተመጣጣኝ ዋጋ በመሙላት እንድትሳተፉ እንገልፃለን።
N.B:- ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
የቤኬ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና
መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-12
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00
- Bid opening: 2026-08-12 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የቤኬ ቅድመ 1ኛ እና አንደኛ ደ/ት/ቤት
- Bid bond: 5000 ብር
- Bid document price: 100 ብር
- Published on: Addis Zemen (Jul 31, 2026)
- Posted at: 2026-07-31T07:45:21.000Z