Addis Ababa

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ የተለያዩ ለምርት አገልግሎት የሚውሉ ጥሬ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሪካል የማሽን መለዋወጫዎች እና መካኒካል የማሽን መለዋወጫዎች መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ 

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ የተለያዩ ለምርት አገልግሎት የሚውሉ ጥሬ ዕቃዎች ፣ ኤሌክትሪካል የማሽን መለዋወጫዎች ፣ መካኒካል የማሽን መለዋወጫዎች ፣

የሎት ቁጥር

የእቃው አይነት

ሎት-1

ለተለያዩ የፕላስቲክ ማምረቻ የሚውሉ ግብዓቶች

ሎት-2

የማሽን መለዋወጫዎች ኤሌክትሪካል ፓርቶች

ሎት-3

የማሽን መለዋወጫ መካኒካል ፓርቶች

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

  1. በኢንዱሰትሪው ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በመምጣት ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾችን መመሪያ እና የዕቃዎችን ዓይነትና መጠን የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
  2. በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ ተጫራቹ የዕቃው ዋጋ በሚለው አምድ ስር የሚሸጡበትን የነጠላ ዋጋ በአሃዝ ያለስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኢንቨሎፕ የኢንዱስትሪው ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በተዘጋጅው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባችሁ።
  3. ተጫራቹ የዕቃዎችን የተናጥል ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል።
  4. ትክክለኛ የተጫራች ስምና አድራሻ በታሸገው ኤንቨሎፕ እና በመጫረቻ ሰነድ ላይ መገለፅ ይኖርበታል።
  5. ተጫራቾች የእቃዎችን ለተቀመጠው የነጠላ ዋጋ ድምር የጨረታ መነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማሰከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
  6. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንዱስትሪው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም።
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ውጤት በኢንዱስትሪው ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከወጣ ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላቸው በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በፁሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥራችን 0116670485/0118592286 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ላይ በየገጹ ስምና ፊርማ ማስገባት አለባቸው።
  10. ተጫራቾች የቫት ሠርተፍኬት፣የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ ሠርተፍኬት እና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ኢንዱስትሪው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. አድራሻችን በመገናኛ ወደ ገርጂ በሚወስደው መንገድ ከአምቼ ዝቅ ብሎ ኒያላ ሞተርስ ፊት ለፊት

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ

አዲስ አበባ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-11
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-11 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ጠዋት በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethio Engineering Group Ethiopia Plastic Industry
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jul 31, 2026)
  • Posted at: 2026-07-31T08:26:08.000Z
← Back to all tenders