Construction consultancy
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በጂንካ አውሮፕላን ማረፊያ (BCO) ቅጥር ግቢ ውስጥ የአውሮፕላን ማኮብኮቢያ መንገድ ላይ ለተከሰቱ መደበኛ ያልሆኑ ሁኔታዎች / ጉድለቶች ዝርዝር ጥናት፣ የምህንድስና ዲዛይን፣ የግንባታ ክትትል እና የውል አስተዳደር አገልግሎት (Consultancy Services for Detail Investigation, Engineering Design, Construction Supervision
Description
የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:-SSNT-T628
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በጂንካ አውሮፕላን ማረፊያ (BCO) ቅጥር ግቢ ውስጥ የአውሮፕላን ማኮብኮቢያ መንገድ ላይ ለተከሰቱ መደበኛ ያልሆኑ ሁኔታዎች / ጉድለቶች ዝርዝር ጥናት፣ የምህንድስና ዲዛይን፣ የግንባታ ክትትል እና የውል አስተዳደር አገልግሎት (Consultancy Services for Detail Investigation, Engineering Design, Construction Supervision and Contract Administration Service for Rurway Pavement Irregularities at Jinka Airport) ብቁ የሆነ ደረጃ አንድ መንገድ ግንባታ ወይም ጠቅላላ ግንባታ ማማከር አገልግሎት የሚሰጡ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ ስራው ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ ለሶስት (3) ወር የዲዛይን ስራ፣ ለአስራ ሁለት (12) ወር የግንባታ ቁጥጥር እና የውል አስተዳደር ስራ እና ለአስራ ሁለት (12) ለጉድለት ተጠያቂነት ጊዜ (Defect Liability Period) ያካተተ ይሆናል፣
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶችና አስፈላጊውን የሰው ሃይል ማሟላት የሚችሉ ሥራ ተቋራጮችን ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1. በዘርፉ ለመስራት ለ2018 ዓ.ም. /2025/2026 እ.አ.አ ከንግድ ሚኒስቴር የተሰጠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
2. በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል ለ2025/2026 G.C / 2018 ዓ.ም የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
3. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ የሚያሳይ ህጋዊ የስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ እና በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የአቅራቢዎችና አገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆን ይገባቸዋል።
4, የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣
5. የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ከታክስ እዳ ነጻ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
6. የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ውስጥ ለመሳተፍ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተሰጠ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
7, ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (100.00 ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E‐99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T628 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላከ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ከፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
8. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ሁለት መቶ ሺህ ብር (200,000.00 ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንክ ዋስትና ወይም በባንከ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና Conditional (ሁኔታዊ የሆነ) የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለአንድ መቶ ሃምሳ (150) የቀን መቁጠሪያ ቀናት የጸና ይሆናል።
10. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ -
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-517- 8953
ጠይሜ ተሰጋ
ኢ-ሜይል: [email protected]
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Tender details
- Deadline: 2026-08-26
- Bid closing time: 15:00
- Bid opening: 2026-08-26 15:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
- Buyer TIN: 0000028498
- Bid bond: 200,000.00 ብር
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 02, 2026)
- Posted at: 2026-08-03T13:14:00.000Z