Aluminium products and installation

የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት የአልሙኒየም በር እና መስኮት እና ሌሎች የግንባታ አቅርቦትና ገጠማ ስራዎች ከእነእጅ ዋጋው በዘርፉ ከተሠማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማስገጠም ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ዋና መ/ቤት አድራሻው ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 03 ባህር ዳር ጤና ጣቢያ ፊት ለፊት ሲሆን በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 01 እየገነባዉ ላለው G+7 ህንጻ የአልሙኒየም በር እና መስኮት እና ሌሎች የግንባታ አቅርቦትና ገጠማ ስራዎች ከእነእጅ ዋጋው በዘርፉ ከተሠማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለ መግዛትና ለማስገጠም ይፈልጋል።

የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ።

1.ተጫራቾች ለበርና መስኮት ገጠማ ሥራ የሚቀርበውን ከሎት 1-3 የተቀመጡትን ስራዎች ዓይነት፣ ብዛትና ዝርዝር አፈፃፀም ከግልፅ ጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያያዘው ስፔስፍኬሽን ሠነድ ላይ በጥንቃቄ መመልከት ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት በስራ ሰዓት ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 03 ባህር ዳር ጤና ጣቢያ ፊት ለፊት ከሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 201 መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር ማሟላት ያለባቸው።

  • በዘርፉ በዘመኑ የተሰጠ ወይም የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው።
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው።
  • የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሠነዱን ዋናውንና ኮፒውን በሁለት የተለያዩና በጥንቃቄ በታሸጉ ፖስታዎች በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 203 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ቅዳሜ እስከ 6፡00 ድረስ ያለውን ቀን ጨምሮ ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነድ በመግዛትና ሰነዳቸውን ሞልተዉ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. የጨረታው አሸናፊው ዉል በሚይዝ ሰዓት ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ፐርፎርማንስ ቦንድ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና አሰርቶ ማቅረብ አለበት።

6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 203 በ22ኛዉ ቀን 4፡00 ታሽጎ በ4፡15 ይከፈታል። ዘግይቶ ጨረታዉ ከታሸገ በኋላ የቀረበ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም።

7. የጨረታ መክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

8. አሸናፊው ያሸነፈበትን ዕቃ ናሙና በቅድሚያ ማቅረብና ድርጅቱ በአማካሪዉ ጥራቱን ካረጋገጠ በኋላ ውል መፈረም ይኖርበታል።

9. የጨረታዉ አሸናፊ እንደ አስፈላጊነቱ ታይቶ በተናጠል ወይም በጥቅል ሊሆን ይችላል።

10. ተጫራቾች በመወዳደሪያ ፖስታቸው ላይ ስም፣ ፊርማ እና የንግድ ድርጅቱን ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. ለተጨማሪ መረጃ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 09 00 86 23 30 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት
ባሕር ዳር


Tender details

  • Deadline: 2026-08-25
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛዉ ቀን 4፡00
  • Bid opening: 2026-08-25 10:15
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛዉ ቀን 4፡15
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara Region Housing Development Agency Office
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Be'kur (Aug 03, 2026)
  • Posted at: 2026-08-04T09:18:32.000Z
← Back to all tenders