Water supply construction
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ወላይታ ዞን የአበላ አባያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ከEU/DDRM ፕሮጀክት ባገኘነው የገንዘብ ድጋፍ በወረዳው በሁለት ቀበልያት በአባይ ጉሩቾ ማዘጋጃ 4 ኪሎ መንደር እና በአበላ ሎንገና ቀበሌ የእንስሳት ጤና ኬላ እና የንፁህ መጠጥ ውሃ መስመር ዝርጋታና የቦኖ ግንባታ በሁለቱም ሎቶች የግንባታ ዕቃ ማቴሪያል/በማቅረብና የባለሙያ ጉልበት ዋ
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2019
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ወላይታ ዞን የአበላ አባያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ከEU/DDRM ፕሮጀክት ባገኘነው የገንዘብ ድጋፍ በወረዳው በሁለት ቀበልያት በአባይ ጉሩቾ ማዘጋጃ 4 ኪሎ መንደር፤እና በአበላ ሎንገና ቀበሌ፣ በሎት 1 የእንስሳት ጤና ኬላ፣ በሎት 2 የንፁህ መጠጥ ውሃ መስመር ዝርጋታና የቦኖ ግንባታ በሁለቱም ሎቶች የግንባታ ዕቃ ማቴሪያል/በማቅረብና የባለሙያ ጉልበት ዋጋ ጭምር የኬላውን ግንባታ ለማድረግና የውሃ መስመር ዝርጋታ፣ የቦኖ ግንባታ ለመሥራት ፈቃደኛ የሆኑና ሙሉ ግንባታውና ሥራውን ማቴሪያል አቅርቦ ገንብቶና ሠርቶ ለማስረከብ የሚችል የግንባታና የውሃ መስመር ዝርጋታ ባለሙያ ኮንትራክተር በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፣
1/ በግንባታም ሆነ በውሃ መስመር ዝርጋታ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ተጨማሪ እሴት ታክስ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ(ች)፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው(ላት)፣የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት ያለው፣አቅራቢነት ያለው (ላት)
በሎት 1/ ለእንስሳት ጤና ኬላ ግንባታ ደረጃው GC/BC 5- እና ከዚያ በላይ
በሎት 2 ለውሃ ዝርጋታ መስመር ደረጃ -5 wwC እና ከዚያ በላይ ያላቸው
2/ ተጫራቾቹ የጨረታ ሠነድ ሲገዙ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር ለእያንዳንዳቸው ሎት በወረዳው ገቢዎች ቢሮ በመሄድ ከፍሎ የጨረታ ማስታወቂያው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 30 ተከታታይ የሥራ ቀን ዘውትር በሥራ ሰዓት ከወረዳው ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት ከግዥና ንብረት አስ/ር ዋና ሥራ ሂደት ቀርበው ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
3/ ለሁለቱ ግንባታና የውሃ መስመር ዝርጋታ በዘርፉ 3/ሶስት/ዓመትና ከዚያ በላይ ሥራ ልምድ ያለው።
4/ ጨረታው በግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀነ ጀምሮ ለተከታታይ 30 የሥራ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኃላ በ31ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ ሰንበት /የበዓል/ ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይሆናል።
5/ ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ከሌሎች አስፈላጊ የመጫረቻ ሠነድ ጋር በታሸገ ኤንበሎፕ ሁለት ኦርጅናልና ኮፒውን ሠነድ ማህተም፤ ስም፤አድራሻ፣ስልክ ቁጥርና ፊርማ በማድረግ ለየብቻ በማሸግ አበላ አባያ ወረዳ ፋይ/ፕላን/ጽ/ቤት ከግዥና ንብረት አስ/ር ዋና ሥራ ሂደት በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን መጨመር አለባቸው።
6/ ተጨራቾች የጨረታ ሠነድ ላይ የሚወዳደሩበት ዋጋ ቫት ያጠቃለለ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡ ካልተጠቀስ ቫት እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
7/ የጨረታ አሸናፊው ውጤት የሚለየው ተጫራቹ በጨረታ ማወዳደሪያ ሠነድ ላይ በዝርዝር የቀረቡት አጠቃላይ ድምር ውጤት ይሆናል።
8/ በጨረታው መወዳደሪያ ሠነድ በዋጋም ሆነ በሌላ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
9/ ሎት 1 እና ሎት 2 ጨረታዎች አሸናፊው ተጨራች የቅድመ ክፍያ ከመቀበሉ በፊት የቅድመ ክፍያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ 30% ከህጋዊ ባንክ ቼክ cpo /ሲፒኦ/ ማቅረብ አለባቸው።
10/ አሸናፊ ተጨራች ሎት 1 እና ሎት 2 ጨረታ የውል ማስከበሪያ የውሉን ዋጋ 10% ከህጋዊ ባንክ ቼክ cpo /ሲፒኦ/ በጀርባው የንግድ ባንክ ማህተም ያለበት ማቅረብ አለባቸው።
11/ ማነኛውንም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት -1 50,000 ብር ለሎት 2 30,000 ብር ከህጋዊ ንግድ ባንክ ጋራንት የተረጋገጠ cpo /ሲፒኦ/ ወይም ቼክ፤ጥሬ ገንዘብ ማቅረብ አለባቸው።
12/ የጨረታው አሸናፊ ድርጅት /ግለሰብ/ ማሸነፉ ከተገለጸበት ጀምሮ በ 7 ቀናት ውስጥ ከአሠሪው መ/ቤት ጋር የግንባታ /የሥራ ውል ስምምነት መግባት አለበት።
13/ ሁለቱም ወገኖች ውሉን ተግባራዊ የማያደርጉበት ሁኔታ ቢከሰት የኢትዮ/ያ ፍትሐብሔር ህግ በሚያዘው መሠረት የሚፈፀም ሲሆን ሌሎች በውሉ አፈፃፀም መሠረት አስፈላጊውን መብትና ግዴታዎችን የሚያካትት ይሆናል።
14/ የሳይት ምልከታ፣የድጋፍ ደብዳቤ ከአሠሪው መ/ቤት ማቅረብ ይኖርበታል።
15/ አሸናፊ ተጫራች ለግንባታና ለውሃ መስመር ዝርጋታ ውል በሚገባው መሠረት የግንባታ ዕቃዎች ወደ ሥራ ቦታ የማቅረብ ግደታ አለበት።
16/ መስሪያ ቤቱ የተሸለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
17/ በጨረታው ዝቅተኛ ዋጋ አቅርቦ ያሸነፈ አሸናፊ ውል ለመግባት ፈቃደኛ ካልሆነ በ2ኛ ደረጃ ያሽነፈው ግለሰብ በመጀመሪያው ዝቅተኛ ዋጋ ለመሥራት ፈቃደኛ ከሆነ ዕድል ይሰጠዋል።
ለበለጠ መረጃ፡ ስልክ+251-913-33-67-12 / +251-9-41-05-51-54 / +251-9-16-71-96-87
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወላይታ ዞን የአበላ አባያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-08
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው በግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀነ ጀምሮ ለተከታታይ 30 የሥራ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኃላ በ31ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-08 14:30
- Bid opening (note): ጨረታው በግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀነ ጀምሮ ለተከታታይ 30 የሥራ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኃላ በ31ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Wolayita Zone Abela abaya woreda FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዳቸው ሎት
- Published on: Addis Zemen (Aug 03, 2026)
- Posted at: 2026-08-04T10:26:18.000Z