Freight and cargo transport

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2019 በጀት ዓመት የጭነት መኪና ከነተሳቢው አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት (Specification) መሰረት አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጭነት መኪና ከነተሳቢው የአገልግሎት ግዥ

ለመፈፀም የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ሥ.ኮ. ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ/ተ.አ.ጥ.ዘ/01/2018

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2019 በጀት ዓመት የጭነት መኪና ከነተሳቢው አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት (Specification) መሰረት አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ ማስረጃ፣ ከትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚ/ር የብቃት ማረጋገጫ፣ በማኅበር የተደራጀ ድርጅት መሆኑን ማስረጃ፣ EGP ሊስት ተመዝጋቢ መሆኑን ማስረጃ እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ጉምሩከ ፊት ለፊት ከአዋሽ ባንክ ጀርባ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ የግብርና ግብዓት አቅርቦት ግቢ በተሽከርካሪዎች አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ ግዥ ከፍል ቀርበው የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።

ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

የጨረታ ዋጋ ለ30 (ሰላሳ) ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል፡፡ ጨረታው ነሀሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግብርና ግብዓት አቅርቦት ዘርፍ የስብሰባ አዳራሽ ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል።

ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- ስልክ 0911 430 066 ወይም 0913 630 237

ፋክስ 0114 421 312

አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-08-14
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-14 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Agricultural Business Corporation
  • Buyer address: ከሳሪስ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ማህበር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 04, 2026)
  • Posted at: 2026-08-04T11:01:49.000Z
← Back to all tenders