Footwear and leather goods

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የሴት የበረራ አስተናጋጅ ሠራተኞች ጫማ አምራች ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል

Description

 የሴት የበረራ አስተናጋጅ ሠራተኞች ጫማ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር SSNT-T633

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የሴት የበረራ አስተናጋጅ ሠራተኞች ጫማ አምራች ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አምራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-

  1. ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች እና በሙያ ዘርፉ ሶስት ዓመት እና ከዚያ በላይ የሰሩ ፣ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277 (E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T633 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ሰባ አምስት ሺህ ብር (75,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ለ120 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ተጫራቾችን የጨረታ ማስከበሪያ ለተጨማሪ ቀን የሚቆይበት ጊዜ እንዲራዘምለት የመጠየቅ መብት አለው።
  4. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ቅጂውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በተለያየ ኢንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ሐሙስ, ነሐሴ 28, 2018 ዓ.ም እስከ ከጥዋቱ 5:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን 5፡30 በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መሥሪያ ቤት በጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

ቅድስት ታሪኩ: በስልክ ቁጥር፡ +251-11 517-8025 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

ኢሜል: [email protected] 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-03
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid opening: 2026-09-03 11:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
  • Buyer TIN: 0000028498
  • Bid bond: 75,000.00 (ሰባ አምስት ሺህ) ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 05, 2026)
  • Posted at: 2026-08-05T07:38:35.000Z
← Back to all tenders