Addis Ababa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የአየር መንገድ ግቢ ውስጥ ለሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ የምርመራ ቢሮ የህንጻ ዲዛይን እና ግንባታ ፕሮጀክት (Design & Construction of Airport Federal Police Investigation Office Building Project) ብቁ የህንጻ ተቋራጭ ተወዳዳሪዎችን ለመጋበዝ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: SSNT-T630
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የአየር መንገድ ግቢ ውስጥ ለሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ የምርመራ ቢሮ የህንጻ ዲዛይን እና ግንባታ ፕሮጀክት (Design & Construction of Airport Federal Police Investigation Office Building Project) ብቁ የህንጻ ተቋራጭ ተወዳዳሪዎችን ለመጋበዝ ይፈልጋል። የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ በ180 የቀን መቁጠሪያ ቀናት ውስጥይሆናል፣
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች፣ አስፈላጊውን የሰው ሃይል፣ ማሽንና የግንባታ ግብዓት ማሟላት የሚችሉ ሥራ ተቋራጮች ስራውን ለማከናወን ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1. በዘርፉ ለመስራት ለ2018 ዓ.ም /2025/2026 እ.አ.አ. ከንግድ ሚኒስቴር የተሰጠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
2. በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል ለ2018 ዓ.ም የተሰጠው፣
3. በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል ለ2025/2026 GC / 208 ዓ.ም የታደሰ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ (GC/BC-1 የሆነ፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
4. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ የሚያሳይ ህጋዊ የስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ እና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የአቅራቢዎችና አገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆን ይገባቸዋል፣
5. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ከታክስ እዳ ነጻ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
6. የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ውስጥ ለመሳተፍ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተሰጠ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (100.00 ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT_T630 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
8. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት አምስት መቶ ሺህ ብር (500,000.00 ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ውስንነት ያለው (Conditional) የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለአንድ መቶ ሃምሳ (150) የቀን መቁጠሪያ ቀናት የጸና ይሆናል።
10. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጨረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-517- 8953
ጠይሜ ተሰጋ
ኢ-ሜይል: [email protected]
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Tender details
- Deadline: 2026-09-07
- Bid closing time: 15:00
- Bid opening: 2026-09-07 15:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
- Buyer TIN: 0000028498
- Bid bond: 500,000.00 ብር
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Aug 05, 2026)
- Posted at: 2026-08-05T08:39:00.000Z