Veterinary equipment and medicines
የቤ/ጉ/ክ/መ ግብርና ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት የእንስሳት መድኃኒት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የቤ/ጉ/ክ/መ ግብርና ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት በተዘዋዋሪ ፈንድ የእንስሳት መድኃኒት ግዥ ለመፈፀም የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ለ2018/19 ዓ.ም በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ፤ ለ2018/19 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት በሀገር ውስጥ ገቢዎች የጨረታ ተሳታፊነት የድጋፍ ደብዳቤ ያለውን፣ የታደሰ የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ያላቸውን
ተወዳዳሪዎች በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
1. ዝርዝር ጨረታውን የያዘ ሠነድ የማይመለስ ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል አሶሳ በቤ/ጉ/ክ/መ/ግብርና ቢሮ በግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
2. የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
3. አሸናፊ ድርጅት የውል ስምምነት ሲፈርም ለውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% ያስይዛል
4. በጨረታው ያልተመረጡ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበረያ የጨረታ አሸናፊ እንደታወቀ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሠነዱን በመግዛት እስከ 16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሆኖ ነገር ግን ቅዳሜ፤ እሁድ እና የሕዝብ በዓል ቀን ላይ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይዘጋል፡፡
7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አሶሳ በሚገኘው በቤ/ጉ/ክ/መ/ግብርና ቢሮ በግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ይሆናል፡፡
8. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- 0577752144 አሶሳ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-08-21
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-21 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Beneshangul Gumuz
- Publishing entity: Benishangul Gumuz Regional State Agricultural Bureau
- Buyer address: አሶሳ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Aug 06, 2026)
- Posted at: 2026-08-06T07:41:35.000Z