Well drilling and boreholes

የደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በቤንች ሸኮ ዞን በጊዲ ቤንች ወረዳ የዲዙ ጉድጓድ ቁፋሮ የፓምፕ ቴስት የአገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

Description

ለፓምፕ ቴስት የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የመ/ቤቱ ሥም : ደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (ደምኮኮ)

የጨረታ አይነት : አገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ

የጨረታ ቁጥር : 003/2018

የደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በቤንች ሸኮ ዞን በጊዲ ቤንች ወረዳ የዲዙ ጉድጓድ ቁፋሮ የፓምፕ ቴስት የአገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት:-

1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች፦

 በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ሆኖ ለተግባሩ

  • ክሬን ያለው (3 ቶንና ከዚያ በላይ)
  • ፓምፕ - 45 KW (Submersible test pump) የሆነ
  • Estimated Discharge-12-15L/S
  • GI PIPE-3" Length 220m & above የሆነ
  • Generator-125 KVA& above የሆነ
  • የግብር ከፋይነት መለያ ሠርቲፊኬት ያላቸው፣
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
  • የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ እና በጨረታ ለመሣተፍ ከገቢዎች ፍቃድ ያላቸው፣
  • ከተለያዩ ተቋማት የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ያላቸው /ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት ጊዜና ቦታ፦

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አሥራ አምስት/ ቀናት ድረስ የማይመለስ ብር 1000.00/አንድ ሺህ ብር/ በኮርፖሬሽኑ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000615509209 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ የንግድ ፍቃዳቸውን ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ ቦንጋ ከተማ 03 ቀበሌ አካባቢ ከሚገኘዉ ቢሮ ከግዥና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

3. ጨረታው የሚከፈትበት እና ሰነዱ የሚቀርብበት ጊዜ፦

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ በመግዛት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል:: የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች አለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት ሂደት አያስተጓጉልም።

4. የጨረታ ዋስትና ፦

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ዋጋ ሁለት ከመቶ /2%/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ከ90 /ዘጠና/ ቀናት ያላነሰ ጊዜ ያለው የባንክ ዋስትና በባንኩ ዋና መ/ቤት የተረጋገጠ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።

5. የጨረታ ሠነድ አቀራረብ ሁኔታ፦

የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢነት የግብር ከፋይነት ሠርቲፊኬት እና የታክስ ክፍያ ማረጋገጫ ሰነዶች፣ በጨረታው ለመሳተፍ ከገቢዎች የተሰጠ ማስረጃ እና የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተደገፈ CPO/ ከዋና /ኦርጂናል የዋጋ ማቅረቢያ ጋር በአንድ ላይ ታሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡  ፋይናንሻል ዶክሜንት ዋና እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።

  • ቴክኒካል ዶከመንት ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።
  •  ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-08-21
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አሥራ አምስት/ ቀናት
  • Bid opening: 2026-08-22 10:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: South West Construction Coorporation
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 1000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 07, 2026)
  • Posted at: 2026-08-07T08:40:03.000Z
← Back to all tenders