Steel raw materials and sections

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለ2018 በጀት ዓመት ለዲስትሪክቱ የመንገድ ጥገናና ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸው የማጠናከሪያ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢመአ/ሻሽ/089/2018

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለ2018 በጀት ዓመት ለዲስትሪክቱ የመንገድ ጥገናና ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸው የማጠናከሪያ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠብቅባቸዋል።

1. ተጫራቾች የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣የምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣የተጨማሪ ታክስ ሰርቲፍኬት እና የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች ለ2017 በጀት ዓመት ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልጽ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።

4. ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በማድረግ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በእለቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት በኃላ ሰዓት ላይ ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል። በእለቱ በዓል ወይም ዝግ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ/በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቁጥር 1000002579859 ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ከሻሸመኔ መንገድ ዲስትሪክት ዕቃ ግዥ/አ ን/አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሰነዱ መግዛት ይቻላል።

7. በጨረታው መክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መስሪያቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0462-114-66 መጠቀም ይችላሉ።

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ የተጠበቀ ነው።

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-24
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን
  • Bid opening: 2026-08-24 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን 8፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 08, 2026)
  • Posted at: 2026-08-08T07:44:39.000Z
← Back to all tenders