Catering and Cafeteria Services

የጉለሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት የካፍቴሪያና የመስተንግዶ አገልግሎት፣ የትራንስፖርት አገልግሎት እና የህትመት አገልግሎት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ የግዥው መለያ ቁጥር 001/2019

  1. የካፍቴሪያ ና የመስተንግዶ አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 130,000.00 ብር(አንድ መቶ ሰላሳ ሺህ ብር)
  2. የትራንስፖርት አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 20,000.00 ብር(ሀያ ሺህ ብር)
  3. የህትመት አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 30000.00 ብር (ሰላሳ ሺህ ብር)

በጨረታው ለመካፈል ተጫራቾቾ

1ኛ, በጨረታ የሚወደዳሩ ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት በስማቸው ያላቸውን የዘመኑን ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የግብር ግዴታቸውን በግብር አስገቢ ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡

2ኛ. ተጫራቾች የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /TIN number/VAT ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡ ወይም ቲኦቲ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ያስፈልጋቸዋል።

3ኛ. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ በብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 21 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ ፡፡

4ኛ. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ኦርጅናል ሰነድ እና ፎቶ ኮፒ ሰነድ በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ የድርጅቱ ስም ማህተም ስልክ ቁጥር እና ፊርማ መኖር አለበት፡፡ የሚጫረቱበትን የዕቃ አይነት በመጥቀስ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት በስራ ሰአት ሶስተኛ ፎቅ በቢሮ ቁጥር 21 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5ኛ, ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህራዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ባበቃ በመጨረሻ ቀን 10፡30 ይታሸግና በማግስቱ 3፡00 ሰአት ይከፈታል፡፡

6ኛ. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ/CPO/ ማስያዝ አለባቸው። እና የጨረታውን አሸናፊ 10% የጨረታው ውል ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

7ኛ. አሸናፊው ተጫራች ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30 እስከ 11፡30 ንብረቶችን በራሱ በማጓጓዝ ማስጫኛና ማውረጃውን ጨምሮ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ፅ/ቤት ግቢ ውስጥ ማውረድ ይኖርበታል፡፡

8ኛ. ጽ/ቤቱ የሚያጫርተውን የዕቃ ብዛት 20 ፐርሰንት መቀነስና መጨመር ይችላል።

9ኛ. መስሪያ ቤቱ ያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጫራቾች ማብራራያ ማስረጃ በስልክ ቁጥር 0111-22-67-04 እና 0118-12-24-04 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

10ኛ. ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረቱበት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው ናሙና ማቅረብ የማይችል ከሆነ ገላጭ እስፔስፍከሽን ማምጣት አለያም እቃውን የሚያሳይ ጥራት ያለው ፍቶ ማምጣት ይኖራባቸዋል፡፡

11ኛ. ለሰራተኛ ካፍቴሪያ አገልግሎት የሚሰጠው ጉ/ክ/ከ/ወ6 /አስተዳደር በሚገኝበት ቅጥር ግቢ ውሥጥ በተዘጋጀው የሰራተኞች ከበብ ሆኖ የቤት ኪራይ ወጪ የመብራት እንዲሁም የውሀ ወጪን ጨምሮ በመስሪያ ቤቱ የሚሸፈን መሆኑን ያሳውቃል፡፡

አድራሻ፡- ሽሮሜዳ ከስላሴ ቤተክርስቲያን በታች ባለው በግራ በኩል መታጠፊያ 500 ሜትር ገባ ብሎ

የጉለሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-19
  • Bid closing time: 16:30
  • Bid closing (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት በ10፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-20 12:00
  • Bid opening (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት ቆይቶ በማግስቱ በ3፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Gulele Sub City Woreda 6 Finance Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 08, 2026)
  • Posted at: 2026-08-08T08:36:26.000Z
← Back to all tenders